
አሜሪካ ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሦስተኛውን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛዋን መሰየሟን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊው ይፋ አደረጉ። አንቶኒ ብሊንከን እንዳሳወቁት ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በሚንጠው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ እንዲሆኑ የሾሟቸው አምባሳደር ማይክ ሐመርን ነው። ብሊንከን የአዲሱ መልዕክተኛ ሐመር ሹመት፣ አሜሪካ ለአካባቢው ዲፕሎማሲያዊ አስተዋጽኦ ለማበርከት ያላትን ቁርጠኝነት ያመለክታል ብለዋል።
Source: Link to the Post