አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ጫና የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 20 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ጫና የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 20 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ያልተገባ ጫናና ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ዋይት ሃውስ ፊት ለፊት እየተካሄደ ነው። “የበቃ ወይም #NoMore” ዘመቻ አካል በሆነው ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ፣ሜሪላንድና ቨርጂንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ኤርትራውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እየተሳተፉ መሆኑን ከሰልፉ አስተባባሪዎች የተገኘ መረጃ ያመለክታል። ሰልፈኞቹ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያና ኤርትራ ላይ እየተከተለ ያለውን የተሳተተ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ እንዲያስተካክልና ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆም ጥሪ የሚያደርጉ መልዕክቶች እያስተላለፉ ነው። ሰልፈኞቹ በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የከፈተውን ጥቃት የሚያወግዙና ለኢትዮጵያ አጋርነታቸውን የሚያሳዩባቸው መፈክሮች እያሰሙ ነው። በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የዳያስፖራ ማህበረሰብና የሲቪክ ተቋማት ተወካዮች፣የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው አፍሪካውያንና ሌሎች የኢትዮጵያ ወዳጆች ንግግር እንደሚያደርጉ ተገልጿል። የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ የሚከተለውን የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ እንዲያስተካልና ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆም ጫና ለማድረግ ሰላማዊ ሰልፉ በዋሺንግተን ዲሲ በቋሚነት በየሳምንቱ እንደሚካሄድ ተገልጿል። በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ ሰላምና አንድነት ማህበር የዋሺንግተን ዲሲ ግብረ ሃይል ከ “በቃ ወይም #NoMore” ዘመቻ አስተባባሪዎች፣ከተለያዩ ተቋሞችና አገር ወዳዶች ጋር በመተባባር ያዘጋጁት ነው። አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ጫና የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ ሀገራት ከተሞች እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply