አሜሪካ በእስራኤል ላይ ለመጣል ያሰብኩትን ማዕቀብ ትቼዋለሁ አለች

ዋሽንግተን በእስራኤል ጦር ላይ ማእቀብ ለመጣል ያሰበችዉን እቅድ መሰረዟን አስታወቀች፡፡

የእስራኤሉ ኔትዛ ይሁዳ የተሰኘዉ ጦር በፍልስጠየማዉያን ላይ የሰባዊ ጥሰት ይፈፀማል በሚል ነበር አሜሪካ ከሰሞኑ ማዕቀብ እንደምትጥልበት የገለጸችዉ፡፡

ይሁን እንጅ ይህንን ሃሳቧን እንደቀየረች ታይስም ኦፍ እስራኤል አስነብቧል፡፡

ወደ እስራኤል ጉዞ የጀመሩት የ አሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶንዮ ብሊንከንም ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡

ኔትዛ ይሁዳ የተሰኘዉ ጦር ከ2 ዓመት በፊት አሜሪካዊ ዜግነት የነበራቸዉን ትዉልደ ፍልስጤማዊ የ 78 ዓመቱን ኦማር አሳድን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል በሚል ክስ ቀርቦበት ነበር፡፡

አናም የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መንግስት በዚህ የጦር ቡድን ላይ ማዕቀብ እንደሚጥል ሲዘት ቆይቷል፡፡

ኔትዛ ይሁዳ ባታሊዮን በ1999 የተመሰረተና ሁሉም ወታደሮቿ ወንዶች ብቻ ናቸዉ፡፡

ጦሩ በዌስት ባንክ ሰማርያና ይሁዳ በስፋት የሚንቀሳቀስ ነዉ፡፡

አባቱ መረቀ
ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply