
አሜሪካ በ15 ተጨማሪ የሩሲያ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጣለች።
የአሜሪካ ግምጃ ቤት እንዳስታወቀው ማዕቀቡ ወደ ወታደራዊ ተቋማት ፈሰስ የሚደረገውን ገንዘብ መጠን በመቀነስ የሩሲያን ወታደራዊ አቅም ለማዳከም አላማ ያደረገ ነው።
የአር ቲ ዘገባ እንዳመለከተው አሜሪካ ማዕቀቡ ወደ ወታደራዊ ተቋማት የሚደርስን የፋይናንስ ድጋፍ እስከ 80% ይቀንሰዋል ብላለች።
የማዕቀቡ ሰለባ የሆኑ ተቋማት ግን በዝርዝር አልተጠቀሱም።
ለአንድ አመት በዘለቀው የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት አሜሪካ በሩሲያ ላይ 2,500 ማዕቀቦችን ጥላለች።
በሙሉቀን አሰፋ
የካቲት 18 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
Source: Link to the Post