
አሜሪካ እና እስራኤል፣ እስራኤል እና አሜሪካ፤ አንቺ ትብስ አንተ ትብስ መባባለቸው ሁለት አገር መሆናቸውን ያስረሳል። ወዳጅነታቸው ጥብቅ ነው። ጆ ባይደን በድርጊትም በንግግርም ይህን አሳይተዋል፤ ገልጸውታልም። በድርጊት የጦር ጄት የሚሸከሙ መርከቦችን ወደ ሜዲትራኒያን ባሕር በማስጠጋት፣ በቃል ደግሞ ቴል አቪቭ ተገኝተው ደግሞ እስራኤልን “በማንኛውም ሁኔታ ከጎንሽ ነን” በተደጋጋሚ ብለዋል።
Source: Link to the Post