አሜሪካ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከነሐሴ 31 ጀምሮ ለቀጣይ 20 አመታት ለጦርነት ምማግደው ዜጋ አይኖረኝም ስትል አስታውቃለች፡፡

ታሊባን  በአፍጋኒስታን ላይ የሚያካሂደውን ጦርነት በማስፋፋት ተጨማሪ ከተሞችን ሲይዝ አሜሪካ በምላሹ የአፍጋኒስታንን ልዑክ ወደ ዶሃ መላኳ ተገልፃል፡፡

የታሊባን ታጣቂዎች የአፍጋኒስታንን አውራጃ ዋና ከተማ፤ የድንበር ከተሞች እና የንግድ መስመሮችን ከያዘች በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ አገሪቷን ለመከላከል የአፍጋኒስታንን የፀጥታ ሀይሎች መላኳ ተገልፃል።

የአፍጋኒስታን ህዝብ የወደፊት ዕጣውን መወሰን እንዳለበት እና አሜሪካ ዜጎቿን ለ20 አመታት ወደ ለጦርነት እንደማታሰማራቸው አስታውቃለች፡፡

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በአፍጋኒስታን የሚገኘው የአሜሪካ ወታደራዊ ተልእኮ እ.ኤ.አ ነሐሴ 31 ያበቃል ብለዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ የአፍጋኒስታን መልእክተኛ ዛልማይ ካሊልዛድ ወደ ኳታር መሄዳቸውን ተከትሎ ታሊባኖች ወታደራዊ ጥቃታቸውን እንዲያቆሙ እና የፖለቲካ እልባት እንዲያገኙ ግፊት ያደርጋሉ ሲል የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።

ዘገባው የፍራንስ 24 ነው

ቀን 05/12/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply