አሜሪካ 12 ንጹሃንን መግደሏን አመነች፡፡የአሜሪካ ጦር በአፍጋኒስታን በወሰደዉ ጥቃት 12 ንፁሃንን እንደገደለ ፔንታጎን አረጋግጧል፡፡ጥቃቱ የተፈፀመዉ ባለፈዉ የፈረንጆች አመት 2021 የአሜ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/jDkwyixj3JabfWdSdosvlCoHaysUOgiKIDKB5J_uBiPgILIVAESWcpjRE2pgQ7IS8MtYZ2nW0rnY7kkWyJN5Ine1ZMS8nmAq6GjnYmrDSA9S3EfplAI7YdY9N6n2aqlNaz7E-qaymhFl3XFlgZViJFUl8LssyncPHN94oRCNvq4Yi6NgSwWvy7yhqpRJC9UKBhQhJZ6_2TBHCL66y8BoHlqVgcQSn8vTFe6Jt9eDrAhfOnL-AB8MQkuyBcv8IbecRkGGDnK7OiEFJDp5TG0JuLd9gzN8QUUmXZKwvAy-pls__KpyW4dfSKrvu1LHdvL35oebCEpbFUjkmpHXJPWjjA.jpg

አሜሪካ 12 ንጹሃንን መግደሏን አመነች፡፡

የአሜሪካ ጦር በአፍጋኒስታን በወሰደዉ ጥቃት 12 ንፁሃንን እንደገደለ ፔንታጎን አረጋግጧል፡፡
ጥቃቱ የተፈፀመዉ ባለፈዉ የፈረንጆች አመት 2021 የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን ሊወጣ ሲል ነዉ ተብሏል፡፡
በጥቃቱ ከተገደሉ ንጹሃን መካከል ሰባቱ ህፃናት መሆናቸዉንም የአሜሪካ መንግስት አስታወቋል፡፡

ፔንታጎን በበኩሉ ለዜጎቹ ህልፈተ ህይወት ሃላፊነቱን እወስዳለሁ ብሏል፡፡
ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ የአሜሪካ ጦር በተለያዩ አገራት በሚወስደዉ ጥቃት በርካታ ንፁሃን እየሞቱ ስለመሆናቸዉ ሪፖርቶች ያመላክታሉ፡፡
ጦሩ ከአፍጋኒስታን በተጨማሪም በሶሪያ በወሰደዉ ጥቃት ከ 20 በላይ ንጹሃን መግደሉን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
የአሜሪካዉ መከላከያ ሚኒስትር ሊዮይድ ኦስቲን ጦራቸዉ እርምጃ ሲወስድ ንጹሃንን ታሳቢ እንዲያደርግ ማሳሰባቸዉን ዘገባዉ አስዉሷል፡፡

በአባቱ መረቀ
መስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply