አምስቱ የጳጉሜን ቀናት “ጳጉሜን በመደመር” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ኹነቶች ታስበው እንደሚውሉ ተገለጸ

ማክሰኞ ነሐሴ 24 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) መንግስት የ2015 የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለሚያከናውናቸው ተግባራት አምስቱ የጳጉሜን ቀናት “ጳጉሜን በመደመር” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ኹነቶች ታስበው እንደሚውሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ደሲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ በ2014 የታዩ ስኬቶችንና የገጠሙ ፈተናዎችን መነሻ በማድረግ አምስቱ የጳጉሜ ቀናት በተለያዩ ኹነቶች ታስበው ይውላሉ ብለዋል።

እየተጠናቀቀ ያለው 2014 ህውሃት፣ አልሻባብ እና ሸኔን ጨምሮ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ኢትዮጵያን በከፍተኛ ደረጃ የፈተኑበት ዓመት ቢሆንም በብዙ ስኬቶች የታጀበም ዓመት ነበር ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ካለፉ ችግሮች ለመማርና የነበሩ ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል መጪው አዲስ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል ብለዋል።

አምስቱ የጳጉሜን ቀናት ጳጉሜን በመደመር በሚል መሪ ቃል ታስበው እንዲውሉ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወስኗል ብለዋል።

ለአምስቱ ቀናት የተለያየ ስያሜ እንደተሰጣቸው የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በዚህም መሰረት፦
👉 ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃድ ቀን

👉 ጳጉሜ 2 የአምራችነት ቀን

👉 ጳጉሜ 3 የሰላም ቀን

👉 ጳጉሜ 4 የአገልጋይነት ቀን እና

👉 ጳጉሜ 5 የአንድነት ቀን ሆኖ ታስቦ ይውላል፡፡

በእያንዳንዱ የጳጉሜን ቀናት ከቀናቱ ስያሜ ጋር የተገናኙ መርሐ ግብሮች እና ተግባራት እንደሚኖሩትም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም፥ 2014 ፈተናዎች የበዛበት፥ ነገር ግን በበርካታ አኩሪ ድሎች የታጀበ እንደነበር መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply