አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከቤልጂየሙ ዋሎኒያ ኢምፖርት ኤክስፖርት ኤጀንሲ የአፍሪካ እና መካለኛው ምስራቅ ሃላፊ ጋር ተወያዩ

አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከቤልጂየሙ ዋሎኒያ ኢምፖርት ኤክስፖርት ኤጀንሲ የአፍሪካ እና መካለኛው ምስራቅ ሃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂየም የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከቤልጂየሙ ዋሎኒያ ኢምፖርት ኤክስፖርት ኤጀንሲ የአፍሪካ እና መካለኛው ምስራቅ ሃላፊ ዴላትሬ ዶሚኒክ ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይታቸው በዋናነት በኢትዮጵያ ባሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በወቅቱም ኤምባሲው እና ኤጀንሲው በትብብር በጋራ መስራት በሚችሉባቸው የትብብር መስኮች ዙሪያ ሃሳብ ተለዋውጠዋል፡፡

ሁለቱ አካላት በተለይም የጋራ የትብብር መስኮችን በመለየት የዋሎኒያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በተመለከተ መረጃ እንዲያገኙ ለመርዳትና በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ሂሩት በወቅቱ በኤጀንሲው ስር ያሉ ባለሃብቶችና ኩባንያዎች ምርጫ ሊሆኑ የሚችሉና በኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ እና ቀዳሚ ስፍራ የሚሰጣቸውን የኢንቨስትመንት አማራጮች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከቤልጂየሙ ዋሎኒያ ኢምፖርት ኤክስፖርት ኤጀንሲ የአፍሪካ እና መካለኛው ምስራቅ ሃላፊ ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply