አምባሳደር ሐሰን ታጁ ከሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አምባሳደር ሐሰን ታጁ ከሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በሴኔጋል የኢትዮጵያ አምባሳደር ሐሰን ታጁ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማኪይ ሳል ጋር ተወያዩ፡፡

ተሰናባቹ አምባሳደር ከፕሬዚዳንቱ ጋር የሁለቱን ሃገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

አምባሳደሩ የኢትዮጵያ መንግስት የጀመረውን ዘርፈ ብዙ ሪፎርም ምን እንደሚመስል አብራርተዋል፡፡

የተጀመረው ሪፎርምም የህወኃት ጁንታ ሊቀለብሰው ሙከራ ማድረጉን የጠቀሱት አምባሳደሩ መንግስት በህግ ማስከበር ዘመቻው የጥፋት ኃይሉን እንዳስወገደው ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በህዳሴ ግድብ እና በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር ዙሪያ መንግስት የሚያራምደውን አቋም አስረድተዋል፡፡

እንዲሁም መጪው ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ መንግስት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡

ፕሬዚዳንት ማኪይ ሳል በበኩላቸው አምባሳደሩ ስላደረጉላቸው ገለጻ አመስግነዋል፡፡

በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ የሚደረገው ድርድርና በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ያለው የድንበር ውዝግብ በሰላም እንደሚጠናቀቅ ተስፋ እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post አምባሳደር ሐሰን ታጁ ከሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply