አምባሳደር ተሾመ የኢትዮጵያ እና ቻይና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ምሥረታን 50ኛ ዓመት አስመልክቶ የተላከ መልዕክት አደረሱ

አምባሳደር ተሾመ የኢትዮጵያ እና ቻይና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ምሥረታን 50ኛ ዓመት አስመልክቶ የተላከ መልዕክት አደረሱ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የኢትዮጵያ እና የቻይና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ምሥረታን 50ኛ ዓመት አስመልክቶ የተላከ መልዕክት አደረሱ፡፡
አምባሳደር ተሾመ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂፕንግ እንዲሁም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ የተላኩ የእንኳን አደረሰን የደስታ መግለጫ ነው ያደረሱት፡፡
መልዕክቱንም በቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝተው ለአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ው ፔንግ ማድረሳቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

The post አምባሳደር ተሾመ የኢትዮጵያ እና ቻይና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ምሥረታን 50ኛ ዓመት አስመልክቶ የተላከ መልዕክት አደረሱ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply