አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከቱርክ አቻቸው ጋር ተወያዩ።

ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ጋር ተወያይተዋል፡፡ የሁለቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውይይት የተደረገው በሩሲያ እየተካሄደ ከሚገኘው የብሪክስ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ነው፡፡ ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አናዶሉ ዘግቧል፡፡ ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply