አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ለተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮችና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ገለጻ አደረጉ

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ለተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮችና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ገለጻ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ለተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮችና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርክ ሎውኩክ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ገለጻ አደረጉ፡፡

በዚህ ወቅትም ሰብዓዊ ድጋፎችን ማቅረብ የሚያስችሉ መንገዶችን መክፈት በሚቻልበት አግባብ ላይ ትኩረት አድርገው መክረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በውይይታቸው ወቅት የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ኢትዮጵያ ተቀራርበው ለመስራት መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

The post አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ለተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮችና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ገለጻ አደረጉ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply