አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከካናዳ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከካናዳ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከካናዳ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ተወያዩ፡፡

አምባሳደር ናሲሴ ከካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ሞሪሰን፣ በካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፓርላማ ጸሐፊ ሮብ ኦሊፋንት እና በካናዳ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ቢሮ የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጊዜያዊ ጀነራል ዳይሬክተር ቤት ሪቻርድሰን ጋር ነው የተወያዩት፡፡

ውይይታቸው በዋናነት በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብና በመጪው ሃገራዊ ምርጫ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በዚህ ወቅትም በትግራይ ክልል እየቀረበ ስላለው ሰብዓዊ ድጋፍ እና እየተካሄደ ስለሚገኘው መልሶ ግንባታን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በክልሉ ባሉ ወቅታዊ ተግዳሮቶች ዙሪያም ተወያይተዋል፡፡

በተጨማሪም ክልሉን በተመለከተ ያልተጨበጡና ፖለቲካዊ ዓላማ ያላቸው የሐሰት መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሚገኙም ለኃላፊዎቹ አስረድተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

The post አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከካናዳ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply