አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ከሩሲያ ምክር ቤት የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ

አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ከሩሲያ ምክር ቤት የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ከሩሲያ ምክር ቤት የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር ኮንስታንቲን ኮሳቼቭ ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያዩ ፡፡
በውይይታቸው አምባሳደር አለማየሁ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸው ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የትግራይ ክልል ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻሉን ጠቅሰው የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ለማረጋጋት፣ በህወሓት ጁንታ የተጎዱ የመሰረተ ልማት አውታሮችን ጠግኖ ወደ አገልግሎት ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን፣ መንግስታዊ አገልግሎቶችን ለማስቀጠል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እየተደረገ ያለው ርብርብ መቀጠሉን እና የሰብዓዊ እርዳታ የማዳረስ ጥረቶችን በተመለከተ ገልፀዋል፡፡
ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር ጉዳይ በተመለከተ ደግሞ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት የሚያስችል ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣ የዲፕሎማሲያዊ መፍትሄን በመጠቀም ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደምትፈልግ እና የተሻለ አማራጭ እሱ ብቻ እንደሆነ በጽኑ እንደምታምንም አረጋግጠዋል ፡፡
የሩሲያ ምክር ቤት የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር በበኩላቸው የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታን በሚገባ መረዳታቸውን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ፈታኝ ሁኔታ ለመወጣት ያደረገችውን ዘመቻ ሀገራቸው ትደግፈዋለች ብለዋል።
እንዲሁም ለአካባቢያዊ ሰላም በአጠቃላይ እና ከሱዳን ጋር በድንበር አካባቢ ያጋጠመውን ጉዳይ በመግባባት መፍታት ቁልፍ መፍትሄ መሆኑንም ጠቁመዋል ፡፡
በሌላ በኩል በሩሲያና በኢትዮጵያ መካከል በፖለቲካ ፣ በንግድ ፣ በኢኮኖሚ ፣ በባህልና በሰብአዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያለውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልፀው በሁለቱ ሃገራት መካከል የፓርላማ ለፓርላማ ትብብር ማጠናከር ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ከሩሲያ ምክር ቤት የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply