አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ በአጊቱ ጉደታ ግድያ ዙሪያ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዘነቡ ታደሠ የተመራው ልዑክ በቅርቡ በድንገት በሰው እጅ ህይወቷ የተቀጠፈው ኢትዮጵያዊት አጊቱ ጉደታ ትኖርበት ወደነበረው አካባቢ በማቅናት በግድያዋ ዙሪያ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር ውይይት አካሄደ።

አምባሳደር ዘነቡ በባለስልጣናቱ ለተደረገላቸው አቀባበል እንዲሁም የአጊቱ ሞት ዜና በተሰማ አጭር ጊዜ ውስጥ የትረንቶ ከተማ ነዋሪ ወጥቶ ላሳየው ፍቅርና የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አምባሳደሯ አክለውም የአጊቱ ገዳይ የምርመራ ሂደት ተጣርቶ ትክክለኛ ፍትህ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

በውይይቱ የተሳተፉት የትረንቶ ከተማ ከንቲባ፣ ፍትህና ፖሊስ ኃላፊዎች የአጊቱ ሞት ሁሉንም የከተማ ነዋሪን ያስደነገጠና ያሳዘነ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአካባቢያቸው በብዙ መልኩ በአርአያነት የምትጠቀስ እንደነበረችም ነው ያስታወሱት።

በተጨማሪም በአጊቱ ሞት ዙሪያ የተጀመረውን የወንጀል ምርመራ ሂደት ቶሎ ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በመጨረሻም አምባሳደሯ አጊቱ ተከራይታ ትሰራበት በነበረው ቤት  በመገኘት የአበባ ጉንጉን ማስቀመጣቸውን በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ በአጊቱ ጉደታ ግድያ ዙሪያ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ጋር መከሩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply