አምባሳደር ፍጹም አረጋ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለካናዳዋ ገዢ አቀረቡ

አርብ መስከረም 20 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በካናዳ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለካናዳዋ ገዥ ሜሪ ሳይመን አቅርበዋል፡፡

አምባሳደር ፍጹም በኢትዮጵያ እና ካናዳ መካለል ያለውን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም አምባሳደሩ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ለካናዳዋ ገዢ ማብራሪያ መስጠታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

The post አምባሳደር ፍጹም አረጋ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለካናዳዋ ገዢ አቀረቡ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply