አምባ ትምህርት ለትምህርት ቤት መገንቢያ ከመንግስት ቦታ ቢሰጠውም እስካሁን የባለቤትነት ሰርተፊኬት አላገኘሁም አለለብዙ አመታት በኪራይ ቤት ሲያስተምር ቆይቶ አሁን ከመንግስት በተደረገለት ድ…

አምባ ትምህርት ለትምህርት ቤት መገንቢያ ከመንግስት ቦታ ቢሰጠውም እስካሁን የባለቤትነት ሰርተፊኬት አላገኘሁም አለ

ለብዙ አመታት በኪራይ ቤት ሲያስተምር ቆይቶ አሁን ከመንግስት በተደረገለት ድጋፍ መሬት ማግኘቱ ታውቋል።

ነገር ግን ለመሬቱ የባለቤትነት ሰርተፊኬት ስላልተሰጠው ለማልማት አለመቻሉ ተነግሯል ።

አምባ ትምህርት   ለተቸገሩ በጎ አድራጎት ማህበር  ይህን ያለው  የመማር እድል የተነፈጋቸውን ህፃናትና አካል ጉዳተኞችን እንድናስተምር እንዲሁም እናቶች እንድንደግፍ ያግዙን በማለት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው።

ኢንፖ አምባ 15 አመት ምስረታ በአሉንም  አክብሯል ።

ከመጀመሪያ ጀምሮ ድርጅቱን ሲደግፉ ለቆዪ አካላትም ምስጋና አቅርቧል ።

ፍቃደኛ በሆኑ በኢትዮጵያ ህፃናት አምባ ውስጥ አድገው አሁን በተለያዮ የስራ መስኮች ላይ በተሰማሩ ግለሰቦች የተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት መሆኑን ተገልጿል።

በተለያዮ ማህበራዊ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ብርሀንን ለማግኘት ላልቻሉ ህፃናት ደረጃውን የጠበቀ የቅድመ መደበኛ እና መደበኛ ትምህርት እንዲያገኙ የማስቻል ስራውች እንደሚሰሩ ተናግሯል።

በሐመረ ፍሬው

መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply