አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማይካድራ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጫለሁ አለ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማይካድራ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጫለሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማይካድራ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች በስለት እንደተገደሉ ማረጋገጡን አስታወቀ።
የድርጅቱ በሳተላይት እና በቀውሶች መረጃ ላቦራቶሪ በተካሄደ ምርመራ በማይካድራ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሰዎች በየቦታው ተጥለው ወይንም ሰዎች በቃሬዛ አስክሬኖችን ተሸክመው ሲንቀሳቀሱ የሚያሳይ ምስል እና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ማግኘቱን ገልጿል።
የተገኙት እነዚህ ምስሎችም የቅርብ ጊዜያት እንደሆኑ ማረጋገጥ መቻሉን ድርጅቱ አስታውቋል።
በርካታ ሰላማዊ ዜጎች መጨፍጨፋቸውን አረጋግጫለሁ ያለው ድርጅቱ፤ በዚህ ጭፍጨፋ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች መንግስት በአካባቢው እየወሰደው ከሚገኘው ህግን የማስከበር እርምጃ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ሰላማዊ ዜጎች መሆናቸውንም ገልጿል።
በርካታ አስክሬን የተገኘው በከተማዋ መሀል መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃቱ የተፈፀመው የመከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ከተማዋን ከመቆጣጠራቸው በፊት ነው ብሏል አምነስቲ በመግለጫው።
ሰላማዊ ዜጎቹ የተገደሉት በተለያዩ የስለት መሳሪያዎች መሆኑን ያስታወቀው አምነስቲ፤ ከአይን እማኞች አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት ግድያውን የፈፀሙት የህወሓት ቡድን የሚመራው የትግራይ ልዩ ሀይል አባላት እና ሚሊሻዎች ናቸው ብሏል።

The post አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማይካድራ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጫለሁ አለ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply