አርማታና ብረት ተደርምሶ በስራ ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው አለፈ። እየተገነባ ባለ ህንጻ አርማታና ብረት ተደርምሶ ሁለት ሰራተኞች ህይወታቸው አለፈ።በአዲስ አበባ ከተማ ጥር 19 ቀን…

አርማታና ብረት ተደርምሶ በስራ ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።

እየተገነባ ባለ ህንጻ አርማታና ብረት ተደርምሶ ሁለት ሰራተኞች ህይወታቸው አለፈ።

በአዲስ አበባ ከተማ ጥር 19 ቀን 2016 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኦርማ ጋራዥ ጀርባ እየተገነባ ባለ ህንጻ ላይ እየተሞላ ያለ አርማታና ብረት ተደርምሶ በስራ ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ላይ የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደተናገሩት የሟቾቹ ዕድሜ 32 እና 35 መሆኑን ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የሟቾቹን አስከሬን ከተጫናቸዉ ፍርስራሽ ስር አንስተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።

የኮንትራክሽን ስራዎች በሚሰሩበት ጊዜ አስሪዎችም ሆነ ሙያተኞች አስፈላጊዉን የደህንነት መርሆዎች ባለመከተል መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ የጥንቃቄዉ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ያሻዋል ሲሉ አቶ ንጋቱ ተናግረዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ጥር 19 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply