አርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የኩላሊት ንቅለ ተከላ ቅድመ ምርመራ ጀመረ።

የኩላሊት ንቅለ ተከላ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በብቸኝነት እየተሰጠ እንደሆነ ይታወቃል።

በኩላሊት ንቅለ ተከላ ወቅት የኩላሊት ሰጪውና ተቀባዩ መስማማታቸውን ለማረጋገጥ የሚደረገው ምርመራ በውጭ ሀገር እንደነበር ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት ግን ይህን ለማስቀረት የኩላሊት ንቅለ ተከላ ቅድመ ምርመራ ጀምረናል ሲሉ የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የምርምርና ፈጠራ ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር አለምሰገድ አብዲሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ይህም ረጅም ጊዜ ይፈጅ የነበረውን ሁኔታ ያቀለዋል ብለዋል።

አርማወር ሀንሰን በ1962 ዓም የስጋ ደዌ በሽታን ለማጥናት የተቋቋመ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ግን ስለ ትቢ፣ ወባ፣ ስጋ ደዌ እና መሰል በሽታዎች ምርምሮችን እየሰራ ይገኛል።

ኢንስቲትዩቱ እስካሁን ከ43 ሺ በላይ የኮቪድ 19 ምርመራ በኢንስቲትዩቱ መደረጉንም ሰምተናል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥር 18 ቀን 2013 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply