አርሜኒያ እና አዘርባጃን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ተስማሙ::አርሜኒያ እና አዘርባጃን ከተከሰተዉ አዲስ ግጭት በኋላ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸዉን የአዘርባጃን መገናኛ ብዙሃ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/cMGHinmTwkIPZEc3dVWhibqkOgL7chBOK6QyzvNrbXAqeiOH12ol29trvgcq86nDZoz5Z2lrPrB8NboOwc7tcmK2yAi4TPLMLZKya86JMPwO2msRzDVYXq3_nnWD8snl9mOa8SaMfw61WGlbKFUG8t12LH56dl0287cuiEwrtTN9eljxDSG909ieLOnhAq-w41_h-srO2-QtArgCEEj13JOMklkFJeoROEV1na7fpwWl-D-paoway3irJedA46mvXqD0zZljyisPZQGXQgT1rNR-FkY7AjRq70LvF_Ys427chd7clbA2x-mLqxcJ1OhVrEkQQZ59YQyQoa9TWVv1wQ.jpg

አርሜኒያ እና አዘርባጃን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ተስማሙ::

አርሜኒያ እና አዘርባጃን ከተከሰተዉ አዲስ ግጭት በኋላ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸዉን የአዘርባጃን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

አርሜኒያ እና ሩሲያ፣ አርሜኒያ ከአዘርባጃን በሚያዋስናት ድንበር ላይ በወታሮች መካከል የተፈጠረዉን ግጭት ለማረጋጋት በጋራ እርምጃዎች ለመዉሰድ መስማማታቸዉን የየርቫን ባስልጣናት ገልጸዋል፡፡

የአርሜኒያ መከላከያ ሚኒስትር ሱሬን ፓፒክያን ከአቻቸዉ ሾይጉ ጋር እንደተነጋሩ እና ሁለታችንም ሁኔታዉን ለማረጋጋት አስፈላጊ እርምጃዎችን ለመዉሰድ ተስማምተናል ብለዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ 2020 በተካሄደዉ የናጎርኖ ካራባክ ክልል ጦርነት ቁጥራቸዉ ያልታወቀ በርካታ የአዘርባጃንና የአርሜኒያ ወታደሮች ለሞት መዳረጋቸዉ ይታወሳል፡፡

የአርሜኒያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣዉ መግለጫ፣ አዘርባጃን በጎሪስ ፤ሶክ እና ጄርሞክ ከተሞች አቅጣጫ በአርሜኒያ ወታደራዊ ቦታዎች የጥይት እሩምታ መክፈቷንና ሰዉ አልባ አዎሮፕላችን እንዲሁም ትላልቅ መድፍ እና የጦር መሳሪያዎችን ተጠቅማለች ብለዋል፡፡

የአአርባጃን ወታደሮችም ተመጣጣኝ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን
ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

በቤዛዊት አራጌ

መስከረም 03 ቀን 2015 ዓ.ም

ለወቅታዊና ታማኝ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናላችንን ይከታተሉን!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply