አርሰናል ማንችስተር ዩናይትድን አሸንፏል!አርሰናል ከአስራ ስምንት አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንችስተር ዩናይትድን በአንድ የውድድር አመት ሁለት የሊግ ጨዋታዎችን አሸንፎታል። አርሰናል ማሸ…

አርሰናል ማንችስተር ዩናይትድን አሸንፏል!

አርሰናል ከአስራ ስምንት አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንችስተር ዩናይትድን በአንድ የውድድር አመት ሁለት የሊግ ጨዋታዎችን አሸንፎታል።

አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ የዘንድሮው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ክለብ ሳምንት ከሚደረጉ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች በኋላ ይታወቃል።

የአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታው ቡድን አርሰናል በዘንድሮው የውድድር አመት በሊግ ምርጥ #ስድስት ክለቦች ጋር ያደረገውን ጨዋታ አልተሸነፈም።

አርሰናል በውድድር አመቱ ሀያ ሰባት ጨዋታዎችን በአሸናፊነት ሲወጣ በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ የክለቡ ትልቅ ድል ሆኖ መመዝገብ ችሏል።

ከሊጉ መሪ አርሰናል በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ ያለውን ቀሪ አንድ ጨዋታ ማክሰኞ ከቶተንሀም ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

በጋዲሳ መገርሳ

ግንቦት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply