You are currently viewing አርሶአደሩን እንቅልፍ የነሳው የአፈር ማዳበሪያ እጥረት! ግንቦት 09 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአማራ ክልል በ2015 ለ2016 የምርት ዘመን ከ1.8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ…

አርሶአደሩን እንቅልፍ የነሳው የአፈር ማዳበሪያ እጥረት! ግንቦት 09 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአማራ ክልል በ2015 ለ2016 የምርት ዘመን ከ1.8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ…

አርሶአደሩን እንቅልፍ የነሳው የአፈር ማዳበሪያ እጥረት! ግንቦት 09 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአማራ ክልል በ2015 ለ2016 የምርት ዘመን ከ1.8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ አርሶ አደሩ መጠቀም እንዳለበት ከክልሉ ግብርና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ይጠቁመናል።ይሁን እና እንደሀገር በተከሰተው የግብዓት እጥረት የተገለፀውን ቁጥር ማዳበሪያ ክልሉ ማቅረብ እንዳልቻለ የተነገረ ሲሆን ክልሉ እቅዱን ከ1.8 ሚሊዮን ወደ 900 ሺህ ኩንታል ዝቅ እንዲያደርግ መገደዱን አሁንም የተከለሰ እቅድ ያሳያል። ችግሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ተከልሶ ከታቀደው ከ900 ሺህ በላይ ኩንታል ማዳበሪያ ክልሉ ውስጥ የደረሰው ገና 300 ሺህ ኩንታል ብቻ ነው። አርሶ አደሮች የአፈር ማዳበሪያ ባለማግኘታቸው ያዘጋጁትን የእርሻ መሬት በዘር ለመሸፈን መቸገራቸውን እያሳወቁ ይገኛሉ። ለአብነት ቃላቸውን የሰጡ በምዕራብ ጎጃም ዞን ፤ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች በቂ የአፈር ማዳበሪያ ባለማግኘታቸው ያዘጋጁትን የእርሻ መሬት በዘር ለመሸፈን ተቸግረዋል። ቄስ ተበባል መኮነን ፤ 2 ነጥብ 5 ሄክታር የእርሻ መሬታቸውን በበቆሎ ፣ በስንዴ ፣ በበርበሬና በጤፍ የሰብል አይይነቶች ለመሸፈን በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጽዋል። ላዘጋጁት የእርሻ መሬትም 6 ኩንታል ዳፕና 4 ኩንታል ዩሪያ በአጠቃላይ 10 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ማዳበሪያ አለማግኘታቸውን አመልክተዋል። የችግሩን አሳሳቢነት ለሚመለከታቸው ተቋማት ቢያሳውቁም ጠብቁ ከማለት ውጭ ምንም ተስፋ የለውም ብለዋል። የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ማቅረብ ካልቻለ የጥራጥሬ ሰብሎች የዘር ወቅት የሚያልፍባቸው መሆኑንና የሚፈልጉትን ያህል ምርት ማግኘት የማይችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ሌላው የዚህ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ምስጋነው ስንሻው ያላቸውን 7 ጥማድ መሬት በቆሎ ፣ በስንዴ ፤ በበርበሬና በጤፍ የሰብል አይነቶች ከፋፍለው ለመዝራት እቅድ ይዘው ማሳቸውን ደጋግመው በማረስና በማለስለስ በዘር ለመሸፈን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። የጥራጥሬ ሰብላቸውን ወቅቱ ሳያልፍ ለመዝራት ቢዘጋጁም የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን ገልፀው መሬታቸው ያለ አፈር ማዳበሪያ ማብቀል ስለማይችል በወቅቱ የአፈር ማዳበሪያ የማይቀርብላቸው ከሆነ ከራሳቸው የምግብ ፍጆታ አልፎ ገበያ ላይ የሚቀርብ ምርት ስለሚጠፋ በመንግስት በኩል ትኩረት ተሰጥቶት በአፋጣኝ ሊቀርብልን ይገባል ብለዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply