አርበኛ ስጦታው ዳኘው/ባሻ እና አርበኛ መብራቱ አረጋ ከበርካታ ወራት የጫካ የእንግልት ቆይታ በኋላ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸውንና በትሕነግ ላይ የተቀዳጁት ድል እጥፍ ድርብ ደስታ እንደፈ…

አርበኛ ስጦታው ዳኘው/ባሻ እና አርበኛ መብራቱ አረጋ ከበርካታ ወራት የጫካ የእንግልት ቆይታ በኋላ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸውንና በትሕነግ ላይ የተቀዳጁት ድል እጥፍ ድርብ ደስታ እንደፈ…

አርበኛ ስጦታው ዳኘው/ባሻ እና አርበኛ መብራቱ አረጋ ከበርካታ ወራት የጫካ የእንግልት ቆይታ በኋላ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸውንና በትሕነግ ላይ የተቀዳጁት ድል እጥፍ ድርብ ደስታ እንደፈጠረላቸው ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሃዲው የትሕነግ ቡድን ልማት ከማምጣት ይልቅ በተለያዩ የወልቃይት ጠገዴና ራያ አካባቢዎች ለዓመታት ሲገነባቸው የነበሩ ምሽጎችን በማፍረስና ጠላትን በመደምሰስ የወልቃይት፣ጠገዴና ራያ ህዝብ ነጻ እንዲወጣ የድርሻቸውን አበርክተዋል፤ በተከፈለው መስዋዕትነትም ታሪካዊ አሻራቸውን አስቀምጠዋል። ጀግኖች አርበኛ ስጦታው ዳኘው/ባሻ እና አርበኛ መብራቱ አረጋ ይባላሉ። ጀግኖቹ ለወራት በጫካ ሆነው ለአማራ ህዝብ ነጻነትና ክብር ማንነትና እርስቱ ይመለስ የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳታቸው በአንዳንድ ፀረ ለውጥ ኃይሎቹ ሲገፉ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ለበርካታ ወራት በጫካ ሆነው ችግሮች በሰላም ይፈቱ፤ እኛ ከመንግስት ጋር ጦርነት ለመግጠም አልታገልነም ሲሉ ተደምጠው ነበር። በመጨረሻም ጊዜው ደርሶ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈፀመበት የአማራ ህዝብ ጩኸት ይሰማ ዘንድ የፈጣሪ ፈቃዱ ሆኖ እብሪተኛው ትሕነግ በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊትና በአማራ ላይ የክህደትና የውድቀት እርምጃውን ወሰደ። ይህ የዘር አጥፊው ትሕነግ እርምጃ መንግስትን ጨምሮ በተለይ የአማራን ህዝብና የመላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን ቁጣ ቀሰቀሰ። መንግስትም ህግ የማስከበር እርምጃው እንዲወሰድ በግልፅ መፍቀዱን ተከትሎ የታፈኑ ወገኖቻችን ለመታደግ ጀግናው የአማራ ፋኖን፣የአማራ ልዩ ሀይልንና ሚሊሻውን የሚቀድም አልተገኘም። በጫካ ሆነው መንግስት አካሄዱን እንዲያስተካክል፤ እኛ አላማችን ንፁሀንን መግደል፣ማሳደድና መዝረፍ አይደለም። ይልቁንስ ዘር እያጠፋ ያለውን የነፍሰ ገዳይ ቡድኑን ትሕነግን/ሕወሓትን ማስተንፈስ፣ የአማራን ህዝብ መብት፣ጥቅምና ፍላጎትን ማስከበር መሆኑን ደጋግመው አሳውቀው ነበር። በሀገር ክህደት ወንጀል የተሰማራውን ትሕነግ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት መልስ ከሰጡትና በመጨረሻም ድሉ የመላው አማራ፣አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንና የፀጥታ መዋቅሩ እንዲሆን በተለያዩ ግንባሮች በመሰለፍ የራሳቸውን አሻራ ካስቀመጡት መካከል ደግሞ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ያነጋገራቸው አርበኛ ስጦታው ዳኘው/ባሻ እና አርበኛ መብራቱ አረጋ ይገኙበታል። ከወራት የእንግልት ቆይታ በኋላ በዛሬው እለት ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከሚወዷቸው ቤተሰቦቻቸውና ከወገኖቻቸው ጋር በሰላም መቀላቀላቸውን ገልፀዋል። ደስታው እጥፍ ድርብ መሆኑን የገለፁት ፋኖዎቹ የወልቃይት፣ጠገዴና ራያ አማራ ለዓመታት ሲደርስባችሁ ከነበረው የከሃዲው ጭቆና በተከፈለው መስዋዕትነት ነጻ በመውጣችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። የወልቃይት፣ጠገዴና ራያ ህዝብ ያገኘውን ነጻነት አስከብሮ እንዲዘልቅ፣መንግስትን ጨምሮ መላው አማራና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያንም ከነጻነት ጎን እንዲቆሙ አሳስበዋል። ከጀግና ፋኖዎችና አርበኞች ስጦታው ዳኘው/ባሻ እና መብራቱ አረጋ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply