አርበኛ እና ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ጀግናው በሞት ከተለየን 4 ዓመት አለፈ። አንጋፋው ጋዜጠኛ እና አርበኛ ደምስ በለጠ ታህሳሰ 13 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር ለህልፈት የተዳረገው፡፡ አንጋፋው…

አርበኛ እና ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ጀግናው በሞት ከተለየን 4 ዓመት አለፈ። አንጋፋው ጋዜጠኛ እና አርበኛ ደምስ በለጠ ታህሳሰ 13 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር ለህልፈት የተዳረገው፡፡ አንጋፋው ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ በአንድ ወቅት ለአርበኞች ሲናገሩ “አርበኞች ቅድመ አያቶቻችሁን አስተውሱ! የአድዋውን የማይጨውን ጦርነት አስታውሱ! በዛ ላይ አባቶቻችሁ የሰሩትን ታሪክ አስታውሱ! ሁልጊዜ!” ብለው ነበርና ልናያስታውሳቸው ወደናል፡፡ አርበኛ ደምስ በአማራ ድምፅ ራዲዮ እያገለገሉ ቆይተው ከ32 ዓመታት በላይ የውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ ወደ ናፈቋት ሀገር ኢትዮጵያ ለሚዲያ ስራ እና ቤተሰብን ለመጠየቅ በመጡ በ3 ሳምንታት ውስጥ ታህሳስ 13 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር ህይወታቸው ባሳዛኝ ሁኔታ ያለፈው። ላለፉት 4 ዓመታት እስካሁንም ድረስ ለሁላችንም ሚስጥሩ፣ ሸፍጡ ገሃድ ባልወጣበት ሁኔታ በምግብ ምረዛ ተገድለዋል። የሚወዷትን ሀገር፣ ወገናቸውን፣ ወቅቱን ተመልክተው ተደራጅተህ መክት ሲሉ የመከሩትን አማራን ብሎም መላ ኢትዮጵያዊያንን በተወለዱ በ56 ዓመታቸው ተሰናበቱ። ነፍስ ይማር! ለመላ ቤተሰብና ለወዳጅ ዘመድ፣ ለአድናቂዎቻቸው፣ ለአርበኞች መጽናናትን ተመኘን። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)

Source: Link to the Post

Leave a Reply