You are currently viewing አርበኛ ዘመነ ካሴን በኃይል በማስገደድ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የተደረገው ሙከራ በአርበኛው እምቢተኝነት ከሸፈ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ/ም          አ…

አርበኛ ዘመነ ካሴን በኃይል በማስገደድ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የተደረገው ሙከራ በአርበኛው እምቢተኝነት ከሸፈ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ/ም አ…

አርበኛ ዘመነ ካሴን በኃይል በማስገደድ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የተደረገው ሙከራ በአርበኛው እምቢተኝነት ከሸፈ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ዛሬ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም የአርበኛ ዘመነ ካሴ የፍርድ ቤት ቀጠሮ እንዳለው ይታወሳል፡፡ ለዚህም አምባገነኑ አገዛዝ ሁለት ዲሽቃ ጠምዶ እና ቀይ ቦኔት በለበሱ ኮማንዶዎች አስከብቦ አርበኛውን በግዴታ ችሎት ለማቅረብ ቢሞክርም አልተሳካለትም፡፡ አርበኛው ባለበት የሰባታሚት ማረሚያ ቤት ላይ በርካታ የጸጥታ ኃይሎች አካባቢውን በመቆጣጠር ውጥረት እንዲነግስ አድርገዋል፡፡ ማረሚያ ቤቱን በውስጥና በውጭ በፖሊስ ቢከቡትም አርበኛው ግን ፍርድ ቤት አልቀርብም የሚለው አቋሙን ስላልቀየረ የተላኩ ኮማንዶዎች ወደመጡበት ተመልሰዋል፡፡ የባህር ዳር ወጣትም ከአርበኛው ጎን ለመቆም ሰባታሚት ማረሚያ ቤት የተገኘ ሲሆን ነገር ግን የማዋከብ እና ወጣቶችንም ወደ ማረሚያ ቤቱ እንዳይጠጉ በመከልከል አምባገነንነታቸውን ሲያሳዩ አርፍደዋል፡፡ በዚህም ብአዴን ባሰማራቸው በርካታ ደህንነቶች እና በመንግስት ታዛዥ ወታደሮች አማካኝነት በአካባቢው የተገኘን አንድ ወጣት አፍነው ወስደዋል፡፡ በአጠቃላይ በሰባታሚት ማረሚያ ቤት ታራሚዎች አይበገሬነት፣ በባህርዳር የነቁ ወጣቶች ትግል እና በአርበኛ ዘመነ ካሴ እምቢ ባይነት በሀይል አስገድዶ ለማቅረብ የተሞከረው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል ሲል አሻራ ሚዲያ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply