You are currently viewing አርበኛ ዘመነ ካሴ አስቀድሞ   የማይቀርብባቸውን ምክንያቶች በደብዳቤ ዘርዝሮ ባሳወቀው መሰረት ዛሬም ፍርድ ቤት አልቀረበም። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ታህሳስ 6 ቀን 2015 ዓ/ም…

አርበኛ ዘመነ ካሴ አስቀድሞ የማይቀርብባቸውን ምክንያቶች በደብዳቤ ዘርዝሮ ባሳወቀው መሰረት ዛሬም ፍርድ ቤት አልቀረበም። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 6 ቀን 2015 ዓ/ም…

አርበኛ ዘመነ ካሴ አስቀድሞ የማይቀርብባቸውን ምክንያቶች በደብዳቤ ዘርዝሮ ባሳወቀው መሰረት ዛሬም ፍርድ ቤት አልቀረበም። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 6 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በባህር ዳር ሰባታሚት እስር ቤት የሚገኘው የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) መሪ አርበኛ ዘመነ ካሴ አስቀድሞ ለባህር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የማይቀርብባቸውን ምክንያቶች በመዘርዘር ባሳወቀው መሰረት በችሎት አልተገኘም። በዚህም መሰረት ታህሳስ 6/2015 በነበረው ችሎት ላይ ባለመገኘቱ ለታህሳስ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ስለመሰጠቱ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገረው ጠበቃ ህሩይ ባዩ ገልጧል። በአርበኛ ዘመነ ካሴ ጉዳይ የመሰረተውን ክስ ዐቃቢ ህግ አሻሽሎ እንዲቀርብም ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል። ከአሁን ቀደም አርበኛው በነጻ የተሰናበትበትን የሰኔ 15 ክስን በተመለከተም ከሰሞኑ መጥሪያ እንደመጣለትና መጥሪያውንም ያልተቀበለ ስለመሆኑ መስማቱን ጠበቃ ህሩይ ለአሚማ ጠቁሟል። በመሆኑም አሁን ላይ አርበኛ ዘመነ ካሴ በሁለት የክስ ጉዳዮች እየተጠየቀ ቢሆንም የማይቀርብባቸውን ምክንያቶች ቀደም ሲል በጽሁፍ ዘርዝሮ ባሳወቀው መሰረት በችሎት እየተገኘ አይደለም። አርበኛ ዘመነ ካሴ የአማራ ህዝብ በተደራጁ እና በታጠቁ ጽንፈኛ አካላት በየጊዜው እየተገደለ፣ እየተሳደደ እና እየተፈናቀለ ነው፤ አማራ የህልውና አደጋ ገጥሞታል በማለት በመሆኑም አማራ በመደራጀት ራሱን ብሎም ሀገሩን ማስከበር አለበት በሚል በተለያዩ አካባቢዎች ሲያነቃ፣ ፋኖን ሲያደራጅ እና ሲያሰለጥን እንደነበር ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply