
አርበኛ ዘመነ ካሴ እንዲፈታ የሚጠይቅ የሶስት ቀን ዘመቻ መጀመሩ ታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት በግፍ እስር ላይ የሚገኘው አርበኛ ዘመነ ካሴ እንዲፈታ የሚጠይቀው የሚዲያ ዘመቻ መጋቢት 11/2015 ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እየተከናወነ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የመጀመሪያው ዙር ዘመቻ እስከ እለተ ረቡዕ መጋቢት 13/2015 የሚቆይ መሆኑን በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት እና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ፍትህ ፈላጊ ወገኖች እያስተላለፉት ካለው መልዕክት አሚማ ለመረዳት ችሏል። በአማራ ህዝብ ላይ በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት ይቆም ዘንድ ብሎም ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በአንድነት እና በሰላም የሚኖሩባት ኢትዮጵያ እንድትቀጥል ጽኑ አቋም በመያዝ የታገለው እና እየታገለም የሚገኘው አርበኛ ዘመነ ካሴ እየተፈጸመበት ካለው የግፍ እስር በአስቸኳይ እንዲፈታ ተጠይቋል። የአማራ ህዝብ ራሱን ብሎም ሀገርን ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ሆኖ ከህልውና ጥፋት ለመታደግ መንቃት፣ መሰባሰብ፣መደማመጥ፣መደራጀት፣መሰልጠን እና መታጠቅም አለበት የሚለው አርበኛ ዘመነ ካሴ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ሰብሳቢ መሆኑ ይታወቃል። አርበኛ ዘመነ ካሴን ጨምሮ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ፋኖዎችን፣ እነ ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊ ታዲዎስ ታንቱን እንዲሁም ሌሎች የግፍ እስረኞችን አሁንም አሳሪው የብልጽግና አገዛዝ እንዲፈታ በተደጋጋሚ በፍትህ ፈላጊ ወገኖች እየተጠየቀ እንደሚገኝ ይታወቃል።
Source: Link to the Post