You are currently viewing አርበኛ ዘመነ ካሴ የልደት ቀኑን አስመልክቶ ከባህር ዳር ወህኒ ቤት መልዕክት በጽሁፍ አስተላልፏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸ…

አርበኛ ዘመነ ካሴ የልደት ቀኑን አስመልክቶ ከባህር ዳር ወህኒ ቤት መልዕክት በጽሁፍ አስተላልፏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸ…

አርበኛ ዘመነ ካሴ የልደት ቀኑን አስመልክቶ ከባህር ዳር ወህኒ ቤት መልዕክት በጽሁፍ አስተላልፏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ሳተናዉ ሚዲያ እንዳጋራው አርበኛ ዘመነ ካሴ ከባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት መጋቢት 5/2015 የልደት በዓሉን አስመልክቶ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፏል:_ መወለዴን እጅግ በጣም እወደዋለሁ። ከሞት ይልቅ መወለድ ግዙፍ ትርጉም አለዉ ብየ አምናለሁ። መሬት ለብዙዎች አትመችም ነገር ግን ወደ መሬት እንደመምጣት ጣፋጭ ነገር የለም። መወለድ ድንቅ የተፈጥሮ ገፅታ እና ስጦታ ነዉ። እዉነት ለመናገር ግን ለመጋቢት አምስት ልዩ ትርጉም መስጠት የጀመርኩት እና የበለጠ የወደድኩት እኔ የተወለድኩበት ቀን በመሆኑ ሳይሆን ጸሃፌ-ትዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የተባለ አንድ በእጅጉ የሚያስገርመኝ ምጡቅ ሰዉ የተወለደበት የተባረከ እለት መሆኑን ካወቅሁ በኋላ ነዉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply