
አርበኛ ዘመነ ካሴ የልደት ቀኑን አስመልክቶ ከባህርዳር ወህኒ ቤት መልዕክት ልኳል። መጋቢት 05 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ መወለዴን እጅግ በጣም እወደዋለሁ። ከሞት ይልቅ መወለድ ግዙፍ ትርጉም አለዉ ብየ አምናለሁ። መሬት ለብዙዎች አትመችም ነገር ግን ወደ መሬት እንደመምጣት ጣፋጭ ነገር የለም። መወለድ ድንቅ የተፈጥሮ ገፅታና ስጦታ ነዉ። እዉነት ለመናገር ግን ለመጋቢት አምስት ልዩ ትርጉም መስጠት የጀመርኩት እና የበለጠ የወደድኩት እኔ የተወለድኩበት ቀን በመሆኑ ሳይሆን ጸሃፌ-ትዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የተባለ አንድ በእጅጉ የሚያስገርመኝ ምጡቅ ሰዉ የተወለደበት የተባረከ እለት መሆኑን ካወቅሁ በኋላ ነዉ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post