አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ በተመለከተ ከአማራ ፋኖ በባህር ዳር የተሰጠ የአቋም መግለጫ‼️ **** የአማራ ህዝብ በትግሉ አበርክቶ ካፈራቸው ዋነኞቹ ውስጥ አንዱ ዘመነ ካሴ ነው። ዘመነ-ነት የትግ…

አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ በተመለከተ ከአማራ ፋኖ በባህር ዳር የተሰጠ የአቋም መግለጫ‼️ **** የአማራ ህዝብ በትግሉ አበርክቶ ካፈራቸው ዋነኞቹ ውስጥ አንዱ ዘመነ ካሴ ነው። ዘመነ-ነት የትግል ምልክት መሆኑ ለእኛ ለፋኖዎቹ እንዲሁም ለመላው የአማራ ወጣቶች ውሎ ያደረ ሐቅ ነው።በተጨማሪም የማንደራደርበት የትግል መሪያችን ነው ። መንግስት ከአርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ ጋር የነበረን የእርቅና ሽምግልና ሂደትም ወደ ጎን በመተው የአማራን ስነ -ልቦና የባህል ስሪት በማይመጥን መልኩ በክህደት ሂደት ጀግናችንን ወደ ወኅኒ ቤት መወርወሩን እናምናለን። በመሆኑም ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን በተመለከተ የአማራ ፋኖ በባህር ዳር የሚከተሉት አቋሞችን ለማሳወቅ እንወዳለን ፦ 1).ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን በተመለከተ የነበረውን የሽምግልና እና እርቅ ሂደት ስትመሩ የነበረ የሐገር ሽማግሌዎች፤ የሐይማኖት አባቶችና ፖለቲከኞች እውነታውን ለሕዝባችን በግልፅ እንድታሳውቁ ስንል እንጠይቃለን። 2).መንግስት ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ላይ የፈጠረውን እስራት በአስቸኳይ በማቋረጥ የአማራ ህዝብ ከዋነኛ ጠላቶቹ ጋር የሚያደርገውን ትግል በድል እንዲወጣ ማድረግ አለበት። ጠላትን በስትራቴጂካልም ሆነ ታክቲካል ዉጊያ ማሸነፍ እየተቻለ የአማራን ዋነኞች በማሰር ህዝባችን ማኅበራዊ እረፍት እንዲያጣ የሚያደርጉ ሂደቶችን መንግስት በቶሎ እንዲያቆም እናሳስባለን። 3).ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን በተመለከተ የሰፈር አጀንዳን ለማናፈስ የምትሞክሩ አውደልዳዬች ከመሰል መንደሬነት አስተሳሰብ በመውጣት ለትልቅ የአማራ ህዝብ ተጋድሎ እንድትተጉ እየጠየቅን ከመሰል ሂደት ተሳትፎ በማትመለሱ ውታፍ ነቃዬች ለሚወሰዱ እርምጃዎች ኃላፊነቱ ለመውሰድ ትገደዳላቹህ። 4).ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ የትግል መምህራችን፣ የፅናት ተምሳሌታችን፣ የአይበገሬነት መንፈሳችን ነው። ከሰፈር የገዘፈ አርማችን፣ ከባህር የሰፋ ዋናችንም ነው።ለእኛ አዲሱ ትውልድ ዘመነ ካሴ የሞትንለት ወልቃይታችን ፣የምን ሞትለት መተከልችን ፣ራያችን እና ደራችን ነው ። በመሆኑም ወንድማችንን እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ሕዝባችን የትግል ተጋድሎ የመጠበቅ ግዴታ አለብን። ስለዚህም መላው የአማራ ፋኖ በባህርዳር አባላት እንዲሁም የፋኖን ትግል ወዳድ አማራ ወጣቶችና ህዝባችን ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን በተመለከተ ለምናደርገው ማንኛውም የትግል ጥሪ ዝግጁ እንድትሆኑ እናሳስባለን። 5).ሐገር መስራችና ወጣኒ መንግስት የሆነውን ️የአማራን ህዝብ በሰፈር፣ ሐይማኖትና ጥቅማጥቅም ሰንሰለት ለመከፋፈል የምትሰሩ ሰዎች ላይ ከስራቹህ እንድትታቀቡ እያሳሰብን፣ ዋኖቻችንን በበሬ ወለደ ስም ማጠልሸት በመክሰስ የፖለቲካና ከርስ ትርፍ ለማግኘት የምትታትሩ ሰዎች ላይ ፋኖ የመዥገር ነቃይነት ግዴታውን እንደሚወጣ ለማሳሰብ እንወዳለን። የትግላችን መዳረሻ የአማራ ነፃነት ነው‼️

Source: Link to the Post

Leave a Reply