“አርበኞች ቅድመ አያቶቻችሁን አስተውሱ! የአድዋውን የማይጨውን ጦርነት አስታውሱ! በዛ ላይ አባቶቻችሁ የሰሩትን ታሪክ አስታውሱ! ሁልጊዜ!” አንጋፋው ጋዜጠኛ እና አርበኛ ደምስ በለጠ በአንድ…

“አርበኞች ቅድመ አያቶቻችሁን አስተውሱ! የአድዋውን የማይጨውን ጦርነት አስታውሱ! በዛ ላይ አባቶቻችሁ የሰሩትን ታሪክ አስታውሱ! ሁልጊዜ!” አንጋፋው ጋዜጠኛ እና አርበኛ ደምስ በለጠ በአንድ…

“አርበኞች ቅድመ አያቶቻችሁን አስተውሱ! የአድዋውን የማይጨውን ጦርነት አስታውሱ! በዛ ላይ አባቶቻችሁ የሰሩትን ታሪክ አስታውሱ! ሁልጊዜ!” አንጋፋው ጋዜጠኛ እና አርበኛ ደምስ በለጠ በአንድ ወቅት ለአርበኞች ከተናገሩት የተወሰደ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ… ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር (ኢፒፒኤፍ) ከተግባር ሊግ ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጀውን ፕሮግራም በምንጭነት በመጠቀም የሚከተለውን አጠር ያለ ዝግጅት ወደ እናንተ ለማድረስ ወደናል። አንጋፋው ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ በ1998 ዓ.ም በኤርትራ ተገኝተው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር (ኢህአግ) አርበኞችን አበረታተዋል። ጋዜጠኛው በአስተሳሰብ የላቁና የተደነቁ ስለመሆናቸው አንደኛው ማሳያ ታላቅ የትህትና የይቅርባይነት መንፈስን የተላበሰ ስብዕና ባለቤት መሆናቸው ነው። ከአርበኞች ጋር በተገናኙበት መድረክ ለኢትዮጵያ ልጆች ከሰሜን እስከ ደቡብና ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ላሉትና በአርበኝነት ለተሰለፉት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ኢህአግ አመራሮችና አባላት ውጭ ባሉት ኢትዮጵያዊያን ስም እጅ ነስተዋል። በኤርትራ መድረክ የተገኙትና ታጋዩም በደስታና በደማቅ አቀባበል የተቀበላቸው አርበኛ ደምስ ንግግራቸውን በየት እንደሚጀምሩ የተቸገሩበት ወቅት እንደነበር አልሸሸጉም። አንጋፋው የብዕር ሰው በኢትዮጵያ ለውጥ እንዲመጣ ፅኑ ፍላጎት ነበራቸው፤ ይህ እውን ይሆን ዘንድም ሌት ተቀን ያላንዳች መሰሰት አቅማቸው በፈቀደ መጠን ሁሉ ዘርፈ ብዙ አስተዋፅኦዎችን አበርክተዋል። አምባገነኖችንና ግፈኞችን በሰላ ብዕራቸው ተችተዋል፣ ለአለም ሁሉ አጋልጠዋል፣ እርቃናቸውን አስቀርተዋል። በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ፍፁም ተቀባይነት እንደሌላቸው በማሳየት አምርረው ታግለዋል። ፍሬም አፍርተዋል። ያላቸው ሰዋዊ ባህርይና ትህትና ለሁላችንም አስተማሪ ነው። ከልብ የመነጨ ትህትና የሰዎችን ልብ በፍቅር እንደምን ይገዛል? በታሪካዊ መድረኩ የተገኙት ጋዜጠኛው በመልካም አንደበታቸውና ቅላጺያቸው ውድ የኢትዮጵያ ልጆች፣እናቶቼ አባቶቼ፣እህቶቼ፣ወንድሞቼ ሲሉ በእውነቱ ሰዋዊነታቸው፣ ትህትናቸው ጎልቶ ይደመጣል። በየጊዜው እየተቀያረ በአቋም አልባነት በፅኑ የሚተቸው አርቲስት ሰለሞን ተካልኝም ኋላ ላይ ተቀይሮ አርበኛ የለም ማለቱ ቢነገርም በ1998 ወደ ኤርትራ በተደረገው ታሪካዊ አርበኞችን የመጎብኘት እና የማበረታታት ጉዞው አካል በመሆን ተገኝቶ ከአርበኞች ፊት ቆሞ ሲያለቅስ ተመልክተናል። በወቅቱ አርበኛ ስለመኖሩማ ምስክሩ በመድረኩ የተገኘው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ታጋይ አንዱ ማሳያ ነበር። ለአርቲስቱ ባይታየውም። የሆኖ ሆኖ ጋዜጠኛ ደምስ አርቲስቱ ስለአርበኞች እምባውን ሲያፈስ ተመልክተው እሳቸውም እምባቸው እየተናነቃቸው መሆኑን በመግለፅ ነገር ግን አሉ “እናንተ ጀግኖች ናችሁ የሚለቀስላችሁ ሳትሆኑ የምታስለቅሱ አንበሶች ናችሁ!” ሲሉ በእኛ ደም ሀገራችን ከካሃዲው የጣሊያን አሽከር ወያኔ ነጻ ትሁን ብለው በዱር ለሚዋደቁት ጀግኖች የኢህአግ አርበኞችን አበረታቱ። “ታላቅ ሀገር አለን። ያች ታላቅ ሀገር…” ይላሉ ጋዜጠኛው በወቅቱ ለ15 ዓመት አሁን ደግሞ ለ30 ዓመታት በወያኔ አረመኔያዊ አገዛዝ መከራዋን እያየች በዘር፣በጎሳ፣በጎጥ እንድንለያይ ተደርገናል በማለት ሀገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ በተፍረከረከው ሲይዙት ጭብጥ ባልሞላው በመሰሪው ወያኔ የገጠማትን ምስቅልቅሎሽ ለታጋዮች ያስረዱት። ወያኔ በጠመንጃ ወደ ስልጣን መምጣቱንና የኢትዮጵያ ህዝብም ከደርግ ውድቀት ማግስት ተመልሶ ወደ ጦርነት ላለመግባት ከፍተኛ ተስፋ እንደነበረው አውስተዋል። ይሁንና በጠመንጃ ወደ ስልጣን የተቆናጠጠው ወያኔ ከስልጣን የሚወርደው በጠመንጃ ብቻ መሆኑን በ1997 ምርጫ ወቅት የፈፀመውን እልቂት በመመልከት የዛሬ 15 ዓመት አስረግጠው ነግረውን ነበር_ታላቁ የብዕር ሰው ደምስ በለጠ። አርበኛ ደምስ በለጠ መላ ሰውነትን በሚለበልበው የኤርትራ ሞቃተማ አካባቢ ሜዳ ላይ በተከፈተው መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግራቸውን እንደቀጠሉ ነው። በንግግራቸውም የታጋዮችን ፊት ሲመለከቱ አብዛኞች ወጣቶች ስለመሆናቸው ተረዱ። እነዚህ ወጣቶች ኢትዮጵያ ት/ቤት ገብተው ቢማሩላት ትፈልግ እንደነበር ግን ደግሞ ያለው የአገዛዙ አመፅና የወንጀል ስራ ታጋዮችን አስገድዶ ዱር ቤቴ እንዲሉ ስለማድረጉ በግልፅ ነግረዋቸዋል። ይህም የሆነው ለታላቂቱ ሀገር ኢትዮጵያ ሲሉ ስለመሆኑ ገለፁ። አርበኛው ሲቀጥሉ ወያኔ ጠመንጃ ባልተሸከመ ህዝብ ላይ መተኮስ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በመላው አለም የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ሁሉ መፍትሄ ይፈልግ እንደነበርና ምንድን ነው መፍትሄው በሚል በእጅጉ ይጨነቅ እንደነበር አስታወሱ። በዚህ መሃል ጀግኖች አርበኞች ስለመገኘታቸው በመግለፅ በዚህም ተስፋቸው እንደለመለመ ተናግረው፤ ይህንም በወቅቱ ይሰሩበት በነበረው ንጋት ራዲዮ እንደሚያስተላልፉላቸው ቃል ገቡ። የወጣቱ ድጋፍ እንዳላቸውም አረጋገጡላቸው_አርበኛው፣ጋዜጠኛው፣የመድረክና የብዕር ሰው ደምስ በለጠ። አርበኞች ለከፈሉትና ለሚከፍሉት መስዋዕትነትም ውለታቸውን ሰው ሳይሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደምትከፍላቸውም ነገሯቸው። “አርበኞች ቅድመ አያቶቻችሁን አስተውሱ! የአድዋውን የማይጨውን ጦርነት አስታውሱ! በዛ ላይ አባቶቻችሁ የሰሩትን ታሪክ አስታውሱ! ሁልጊዜ!” ሲሉም መከሯቸው። ቀጥለውም “የጨበጣችሁትን ሰደፍ ወያኔ ላይ ስታነጣጥሩ ያ ክብሩን የጠበቀ ህዝብ በማንም ወራዳ ባለጌ ድኩማን እንደ መለስ ባለ ሲዋረድ እናንተን የመሰለ ልጆች ተፈጥረዋልና እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ታድጓታል። በጣም በጣም እምነት አለኝ በእናንተ።” ነበር ያሉት። አያይዘውም ዋሽንግተን ዲሲ ሲደርሱ የአርበኛውን ልብስ ለብሰው ከአውሮፕላን በመውረድ መልዕክታቸውን ለማስተላለፍ በበኩላቸው ቃል ገቡላቸው። በመጨረሻም በደማቅ ጭብጨባ ታጅበው ታላቁን እውነት መሰክረው ታጋዩን በአካል ተለዩት። ይኸውም “ሀገራችን ኢትዮጵያ ታላቅ ታሪክ ያላት፣ በቅኝ ያልተገዛች፣ሀይማኖቷንና ክብሯን ጠብቃ የኖረች ሀገር ነች። የእናንተ አባቶች፣የእናንተ ቅድመ አያቶች ናቸው ያችን ሀገር ነጻነቷን ጠብቀው የኖሩት፣እናንተም ልጆቿ አርበኞቹ ይህን ለመስራት ዝግጁ በመሆናችሁ ከልብ ከልብ ውጭ ባለው ኢትዮጵያዊ ስም ዝቅ ብዬ አመሰግናችኋለሁ” ነበር ያሉት_ጋዜጠኛ እና አርበኛ ደምስ በለጠ። አርበኛ ደምስ በአማራ ድምፅ ራዲዮ እያገለገሉ ቆይተው ከ32 ዓመታት በላይ የውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ ወደ ናፈቋት ሀገር ኢትዮጵያ ለሚዲያ ስራ እና ቤተሰብን ለመጠየቅ በመጡ በ3 ሳምንታት ውስጥ ታህሳስ 13 ቀን 2011 ዓ.ም የዛሬ 2 ዓመት እስካሁን ለሁላችንም የውስጥ ህመም በሆነበትና ሚስጥሩ፣ ሸፍጡ ገሃድ ባልወጣበት ሁኔታ በምግብ ምረዛ ተገድለዋል። የሚወዷትን ሀገር፣ ወገናቸውን፣ ወቅቱን ተመልክተው ተደራጅተህ መክት ሲሉ የመከሩትን አማራን፣መላ ኢትዮጵያዊያንን በተወለዱ በ56 ዓመታቸው ተሰናበቱ። ነፍስ ይማር! ለመላ ቤተሰብና ለወዳጅ ዘመድ፣ለአድናቂዎቻቸው፣ለአርበኞች፣ ለአማራ ድምፅ ራዲዮ የስራ ባልደረቦቻቸው ሁሉ መፅናናትን ተመኘን። አማራ ሚዲያ ማዕከል! ታህሳስ 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply