You are currently viewing አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ከተኛበት በድንገት ተዝለፍልፎ በመውደቁ ህይወቱ ባለፈው የ3ተኛ ዓመት ተማሪው የተሰማውን ሀዘን ገለጸ፤ አሟሟቱ የበለጠ እንዲጣራ እየተደረገ መሆኑንም አስታውቋል። አማራ…

አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ከተኛበት በድንገት ተዝለፍልፎ በመውደቁ ህይወቱ ባለፈው የ3ተኛ ዓመት ተማሪው የተሰማውን ሀዘን ገለጸ፤ አሟሟቱ የበለጠ እንዲጣራ እየተደረገ መሆኑንም አስታውቋል። አማራ…

አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ከተኛበት በድንገት ተዝለፍልፎ በመውደቁ ህይወቱ ባለፈው የ3ተኛ ዓመት ተማሪው የተሰማውን ሀዘን ገለጸ፤ አሟሟቱ የበለጠ እንዲጣራ እየተደረገ መሆኑንም አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ተማሪ አየለ አካሉ ከእናቱ ወ/ሮ ሙሉነሽ መርሻ እና ከአባቱ ከአቶ አካሉ ወልደኪዳን በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ ሰላ ድንጋይ ፍላገነት ቀበሌ በ1991 ዓ/ም ነበር የተወለደው፡፡ ተማሪ አየለ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በወረዳው እምቧይ ባድ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን በሳሲት አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም የመሰናዶ ትምህርቱን በሰላ ድንጋይ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ተከታትሏል፡፡ ተማሪ አየለ በ2012 ዓ/ም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተመድቦ በግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ‹‹Rural Development and Agricultural Extension›› የትምህርት ክፍል በአግሮ ኢኮኖሚ ትምህርት መስክ ትምህርቱን በመከታተል ላይ ነበር፡፡ የ3ኛ ዓመት ተማሪ የነበረው ተማሪ አየለ በ2015 ዓ/ም መጨረሻ ከሚመረቁ ተማሪዎች መካከል አንዱ ነበር፡፡ ተማሪ አየለ የካቲት 7/2015 ዓ/ም በጧት የነበረውን ገለጻ በማጠናቀቅ ምሳውን ተመግቦ ወደ ዶርሚተሪው ተመልሶ መኝታው ላይ ዕረፍት ላይ ባለበት ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ከዚህ በፊትም በተለይ በፈተና ጊዜያት በሚጥለው ሕመም ዓይነት ከተኛበት በድንገት ተዝለፍልፎ ወደቀ። በወቅቱም የዶርም ጓደኞቹ በአቅራቢያ ወዳላው ነጭ ሣር ሆስፒታል በፍጥነት በማድረስ ሕይወቱን ለማዳን ጥረት ቢደረግም የተማሪው ሕይወት ማለፉ በሆስፒታሉ ተረጋግጧል፡፡ ቀጥሎም የተማሪው አስከሬን አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ተልኮ በተደረገው የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ የሞቱ መንስዔ የምግብ ችግር አለመሆኑ ተረጋግጧል ብሏል። በመቀጠልም በዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል የአስከሬን ምርመራ ተደርጎ ውጤቱ በቀጣይ እንደሚገለጽ በተነገረው መሠረት የተማሪው አስክሬን ወደቤተሰቦቹ ተሸኝቷል፡፡ በመጨረሻም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተማሪ አየለ አካሉ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን በመግለጽ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና ጓደኞች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply