አርቲስት ታሪኩ ጋንካሲ መታሰሩን በመግለፅ የተሰራጩ መረጃዎች የተሳሳቱ ናቸው! “ድሽታ ግና” በሚለው የሙዚቃ ስራው የሚታወቀው አርቲስት ታሪኩ ጋንካሲ ከቀናት በፊት በደቡብ ኦሞ ዞን ጅንካ ከ…

አርቲስት ታሪኩ ጋንካሲ መታሰሩን በመግለፅ የተሰራጩ መረጃዎች የተሳሳቱ ናቸው!

“ድሽታ ግና” በሚለው የሙዚቃ ስራው የሚታወቀው አርቲስት ታሪኩ ጋንካሲ ከቀናት በፊት በደቡብ ኦሞ ዞን ጅንካ ከተማና አካባቢው ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ ስለመታሰሩ የሚገልጹ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወሩ ተመልክተናል።

በደቡብ ኦሞ ዞን የአሪ ብሔረሰብ በዞን የመደራጀት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከቀናት በፊት በዞኑ ዋና ከተማ ጅንካና አካባቢው በተፈጠረ ሁከት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ በተለያየዩ ሚዲያዎች መዘገቡ ይታወቃል።

ኢትዮጵያ ቼክ የመረጃውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ አርቲስት ታሪኩን ያነጋገረ ሲሆን የተሰራጨው መረጃ “ውሸት” መሆኑንና አለመታሰሩን አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ቼክ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የደቡብ ኦሞ ዞን ፖሊስን ያነጋገረ ሲሆን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ሻለቃ ዮሃንስ አርቲስት ታሪኩ አለመታሰሩን አረጋግጠዋል።
ስለ ጉዳዩ ዘናጭ የሬድዮ ፕሮግራም ከአርቲስት ታሪኩ ጋንካሲ ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን ያድምጡ!

https://www.youtube.com/watch?v=Y78NAk-EKZE&t=95s

ሚያዝያ 08 ቀን 2014 ዓ.ም

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply