አርኪ ሆምስ ኤክስፖ ለሁለተኛ ግዜ ሊካሄድ ነው” አርኪ ሆምስ ኤክስፖ” የተሰኘውን በአይነቱ ልዩ የሆነ ኤክስፖ የሚያዘጋጀው አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ነው።” ይህን ሳያዩ ቤት አንዳይገዙ” በ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/lLmAqoh5JaddjzVo6vk9mwvDz8LzWiAl0ErLfjhN-AZi7UtY5PP9Jq2CI7nT5oVykTrw-XmtnJ-_sjip1E145GNSveK6hjTEApNz7xP04Ex_gx5Wkvz1ToQNKySJME8oxAKLjuWOraLGheeTjqvAOWH4cfjS5SHVUgUcFef6hWm6zNTFMLCmUhzaDjLn4dTzJSUV0gutqvOkfvmjOcPoDqbZ0BnNQQvETMOfXIWnnay2F7vQM14KWjQzf5lTjNz8_hvIFfskWhvkqNmPXmXzI7xIQb01UxbRvuxoWfiEOh-m04MBo3ODmIna5HiYqWj3CGxGap39kXxwOesaJe6qSg.jpg

አርኪ ሆምስ ኤክስፖ ለሁለተኛ ግዜ ሊካሄድ ነው

” አርኪ ሆምስ ኤክስፖ” የተሰኘውን በአይነቱ ልዩ የሆነ ኤክስፖ የሚያዘጋጀው አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ነው።
” ይህን ሳያዩ ቤት አንዳይገዙ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ይህ ኤክስፖ ከየካቲት 15 እስከ 17 በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል።

በቤት ግንባታ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች ከቴክኖሎጂ አሰራር ስርዓትና ፕሮጀክት ውጤታማነት አንጻር እርስ በርስ ልውውጥ የሚያደርጉበት እንደሚሆንም ይጠበቃል ።

በዚህ ኤክስፖ ላይ የሪል ስቴት አልሚዎች ቤቶቹን በማቅረብ በፋይናንስ በኩል ደግሞ ባንኮች ይሳተፉበታል ።

በተጨማሪ በኢንቴርየር ዲዛይን (ቤት የማስዋብ አገልግሎት)ላይ የተሰማሩ እንዲሁም የእንጨት ስራ ውጤቶችን የሚያቀርቡ ፈርኒቸር ቤቶች ይሳተፋሉ።
ይህም ሁሉም በአንድ ቦታ በማካተት ቤት መግዛት የሚፈልገውን ሰው ራስ ምታት ያቀላል። ቤት ለመግዛት ፍላጎት ያለው ሰው ዋጋን ጥራትንና ሌሎችንም መረጃዎችን ለማሰባሰብ የሚያባክነውን ጊዜና ጉልበት ይቆጠባል።

ዘርፉ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝም በዚሁ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ሌሎች የኤክስፖ ድምቀቶች ናቸው።
እነዚህ ድርጅቶች ግብይትን ከማዘመን እና የቤት አስተዳደር ስርዓትከማቅለል አንፃር የሚጫወቱት ሚና እጅግ ጉልህ እንደሆነ ይታመናል።

በዚህ ኤክስፖ አቅምን ታሳቢ በማድረግ ታላቅ ቅናሽ ያደረጉ ሪል ስቴቶች ይገባሉ።
በተጨማሪም ለቤት ፈላጊዎች የሚሆኑ ቅንጡ አፓርትመንቶች ከቪአይፒ መሰተንግዶ ጋር ይቀርብበታል።

እንዲህ አይነቱን ኤክስፖ በርካታ ሃገራት ከቤት ግብይት አንጻር እንደ አንድ ኢኮኖሚ ማንቀሳቀሻ ቢጠቀሙበትም በእኛ ሀገር ግን ብዙም የተለመደ አለመሆኑ ተገልጧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 25 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply