
የኮንስትራክሽን ፤የቤት ሻጮችና ገዢዎች፤ አንዲሁም ገንቢዎችና የተለያዩ ተቋማትን ለማገናኘትና ለማስተሳስር እድል የሚሰጠው አርኪ የሪል እስቴት ኤክስፖ በዛሬው እለት ተከፍቷል።
ከዛሬ ግንቦት 5 እስከ 7 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በሚዘልቀው ኤክስፖ፤ በርካታ የቤት አልሚዎች እየገነቡት ያሉት ቤቶች የሚገኙበትን ደረጃ ፣ የቤቶቹን ዋጋ ፣ ሊገነቡት ስላቀዱት ቤት ፣ ስለሚፈልጉት እቃ እና አገልግሎት ከኤክስፖ ተሳታፊዎችና ጎብኚዎች ጋር መረጃና ልምድ ይለዋወጣሉ ተብሏል፡፡
አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ባዘጋጀው በዚህ ኤክስፖ ላይ ለሽያጭ ባለሙያዎች ነፃ ስልጠና እንደሚሰጥና የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱ ታውቋል፡፡
Source: Link to the Post