አርጀንቲናው የዓለማችን እግር ኳስ ጥበበኛ ማራዶና ህይወቱ አለፈ።እንደ ጎርጎሮሲያውያን ዘመን አቆጣጠር 1960 በቦነስ አይረስ ከተማ የተወለደው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ዛሬ ምሽት ህይወቱ ማለ…

አርጀንቲናው የዓለማችን እግር ኳስ ጥበበኛ ማራዶና ህይወቱ አለፈ።

እንደ ጎርጎሮሲያውያን ዘመን አቆጣጠር 1960 በቦነስ አይረስ ከተማ የተወለደው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ዛሬ ምሽት ህይወቱ ማለፉን ዴይሊ ሜይል ዘግቧል።

የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ማራዶና በልብ ህመም ምክንያት በተወለደ በ60 ዓመቱ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል።

ማራዶና በባርሴሎና እና በናፖሊ እግር ኳስ ቡድኖች በርካታ ዋንጫዎችን በማንሳት የማይረሱ የእግር ኳስ ጊዜያትን ማሳለፉ ይታወሳል።

በአቤል ጀቤሳ
ሕዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply