
ድራማዊ ነው በተባለለት የፍጻሜ ጨዋታ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ታላቁን የዓለማችን የእግር ኳስ ውድድር አሸናፊ ሆነ። ልብ በሚያንጠለጥል ሁኔታ አርጀንቲና በመሪነት ጀምራ ፈረንሳይ አቻ እየሆነች ጨዋታው ከመደበኛው ሰዓት ወደ ጭማሪ ሰዓት ዘልቆ ነው በመለያ ምት የተለየው። በአረቡ ዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ በባሕረ ሰላጤዋ አገር ኳታር የተስተናገደውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ አርጀንቲና ያነሳችው ተቀናቃኟን ፈረንሳይን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው።
Source: Link to the Post