አሰልጣኝ እንድርያስ ብርሃኑ የኢትዮጵያ ከ17ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አሰልጣኝ እንድርያስ ብርሃኑ የኢትዮጵያ ከ17ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ እንድርያስ ብርሃኑ የኢትዮጵያ ከ17ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ መድን የቀድሞ ከ17 ዓመት በታች እና የአሁን ከ20ዓመት በታች አሰልጣኝ እንድርያስ ብርሃኑን የኢትዮጵያ ከ17ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን  ዋና አሰልጣኝ በማድረግ  ሾሟል፡፡

በዚህም ፌደሬሽኑ አሰልጣኙን የአንድ አመት ውል አስፍርሟል።

ቡድኑ በታህሳስ ወር በሚጀመረው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሳታፊ መሆኑ ታውቋል፡፡

አሰልጣኝ እንድርያስ ብርሃኑ የኢትዮጵያ መድን ከ17ዓመት በታች ቡድን በ2011ዓ.ም የተሻለ ተፎካካሪ እንዲሆን ማድረጋቸው እንደሚታወስ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

The post አሰልጣኝ እንድርያስ ብርሃኑ የኢትዮጵያ ከ17ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply