አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ተሰናበቱ፡፡የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እና ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ጋር ያለው…

አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ተሰናበቱ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እና ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ጋር ያለው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ በይፋ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው በ2013 የተሾሙት አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል በአራት ዓመታት ቆይታቸው ቡድናችን በ2022 እና 2024 የዓለም ዋንጫ ማጣርያዎች እስከ መጨረሻው ዙር አድርሰዋል፡፡

በ2022 በዩጋንዳ የተሰናዳው የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ዋንጫ ውድድር አሸናፊ እንዲሆን አስችለዋል።

ከ20 ዓመት በታች ቡድኑ በተጨማሪ ከግንቦት 2014 ጀምሮ የዋናው ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) አሰልጣኝ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን በቆይታቸውም የሴካፋ ሴቶች ዋንጫን በ3ኛ ደረጃ እንዲያጠናቅቅ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ፍሬው በቆይታቸው ላበረከቱት ከፍ ያለ አስተዋፅኦ ከልብ የመነጨ ምስጋናውን እያቀረበ በቀጣይ የእግር ኳስ የሥራ ዘመናቸው መልካሙን ሁሉ ይመኛል።

ምንጭ፡- የኢ.እ.ፌ.
ጥር 29 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply