“አሲና ገና” ኤክስፖና ባዛር በዛሬው ዕለት ይከፈታል

    “አሲና ገና” ኤክስፖና ባዛር በዛሬው ዕለት ይከፈታል

  በዲሲቲ  ኢንተርቴይመንትና ኤቨንትስ የተዘጋጀውና ከ500 በላይ የአገር ውስጥና የባህር ማዶ አምራቾችና ነጋዴዎች የሚሳተፉበት “አሲና ገና” የተሰኘው የገና ኤክስፖና ባዛር በዛሬው ዕለት የሚከፈት ሲሆን፤ እስከ ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓ.ም  በኤግዚቢሽን ማእከል ይካሄዳል፡፡
“አሲና ገና” 2015 ኤክስፖና ባዛር፤ የተለያዩ ሸቀጦች ለሸማቾች የሚቀርቡበት የንግድ ትርኢት ሲሆን በየዕለቱ በ10ሺ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ የሚጠበቅና ከፍተኛ የንግድ ልውውጥና ግብይት የሚካሄድበት ዓመታዊ ባዛር ነው ተብሏል። ለ21 ተከታታይ ቀናት በሚዘልቀው በዚህ የንግድ ትርኢት፣ ከ50 በላይ አንጋፋና ወጣት ተወዳጅ ድምጻውያን የሚሳተፉበት የሙዚቃ ኮንሰርት የሚቀርብ  ሲሆን በተጨማሪም ታዳሚውን ባለእድል የሚያደርጉ እጣዎችና አጓጊ ሽልማቶች መዘጋጀታቸው ታውቋል፡፡ በትርኢቱ የወላጆችና ህጻናትን ፍላጎት  የሚያሟሉ የተለያዩ መዝናኛዎችና ጌሞችም እንደተካተቱ ተነግሯል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply