አሳዛኝ ሰበር ዜና! በሆሮ ጉድሮ ዞን ቀድሞ መረጃ የደረሳቸው  የጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ አመራሮች ሀይል ባለመላካቸው የተነሳ 13 የሚሆኑ አማራዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በጥይትና በስለት በግፍ…

አሳዛኝ ሰበር ዜና! በሆሮ ጉድሮ ዞን ቀድሞ መረጃ የደረሳቸው የጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ አመራሮች ሀይል ባለመላካቸው የተነሳ 13 የሚሆኑ አማራዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በጥይትና በስለት በግፍ…

አሳዛኝ ሰበር ዜና! በሆሮ ጉድሮ ዞን ቀድሞ መረጃ የደረሳቸው የጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ አመራሮች ሀይል ባለመላካቸው የተነሳ 13 የሚሆኑ አማራዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በጥይትና በስለት በግፍ ተገደሉ፤ በርካቶች አድራሻቸው አልታወቀም። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሮ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ደርጌ ኮቲቻ በተባለ ቀበሌ የሚኖሩ 13 የሚሆኑ የ4 አባዎራ ቤተሰቦችን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከፊሎችን በአሰቃቂ መልኩ አንበርክከው በጥይት ረሽነዋል፤ ቀሪዎችን ሴትና ህጻናት በገጀራ፣በቆንጨራ እና በካራ እንዳረዷቸው ነው ከአሸባሪዎች ጥቃት ያመለጡ ነዋሪዎች የተናገሩት። ጭፍጨፋው የተፈፀመው ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ባለው ጊዜ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች ገብተው ከፊሎቹ በአካባቢው ነዋሪ በሆኑ የአማራ ሚሊሻዎች ላይ ተኩስ ሲከፍቱ ሌሎቹ ደግሞ በተቃራኒ አቅጣጫ በመግባት በአካባቢው ለዘመናት ነዋሪ የሆኑ 4 አባዎራዎችን ጨምሮ 13 ቤተሰቦቻቸን ልዩ ስሙ ቱሉኮርማ በተባለ ጎጥ ላይ በግፍ ጨፍጭፈዋል። በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በተባባሪዎቹ በግፍ የተገደሉት አማራዎችም:_ 1) ካስዬ ባዬ ከእነ 5 ቤተሰቡ 2) ይብሬ አድማሱ ከእነ 6 ቤተሰቡ 2.1) የይብሬ አድማሱ ባለቤት በለጠች ጎባው፣ 2.2) አሚድ ኢብራሂም፣ 2.3) መካ ኢብራሂም፣ 2.4) ሀሰን ኢብራሂም፣ 2.5) አህመድ ኢብራሂም 3) ሙሳ ደርሶ ናቸው። ከተገደሉት መካከልም 2 አዛውንቶች ሲገኙበት አብዛኞች እናቶችና ህጻናት ናቸው፤ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተጠቁሟል። በተጨማሪም የ7 ኛ ክፍል ተማሪው ሀሚድ ይብሬ ቆስሎ ህክምና ባለማግኘቱ ከሌሊቱ 10:30 ሰዓት ላይ ህይወቱ አልፏል፤ ሀሰን ይብሬ የተባለ አባትም ታፋው ላይ በጥይት ቆስሎ እየተሰቃዬ ይገኛል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የአቶ አህመድ ገዳሙ 7 ቤተሰብ፣ የእስሌማን መሀመድ 13 ቤተሰብ፣የአቶ ፈንታው አያሌው 7 ቤተሰብና ሌሎችንም እስካሁን የት እንዳደረሷቸው ለማወቅ አልተቻለም ብለዋል። ለሚሊሻ ተብሎ ከላይ የሚላከው ጥይትም ለኦነግ ሸኔ ተላልፎ እንደሚላክ ፤ ለሚሊሻዎች ግን ቀናንሰው 4 እና 5 ጥይት ብቻ እንደሚሰጧቸው ነው ምንጫችን የገለፁት። ቱሉኮርማ በተባለ አካባቢ ያገኙትን ወጣት አደም ካሳዬ ከቀኑ 12 ሰዓት ጀምሮ አስረው በማቆየት ምሽት ላይ የአማራን ቤት አሳዬን በማለት አስገድደው እንዲመራ እና ሰዎችን እንዲጠራ አድርገውታል፤ አሰልፈው ሲረሽኑ ወጣቱ ሮጦ ማምለጡ ተገልጧል። በጃርዴጋ ጃርቴ እና በአሙሩ ወረዳዎች በቅርቡ እንኳ ለ4ኛ ጊዜ ነው የአማራ ተወላጆች በጅምላ የተጨፈጨፉት ያሉት ነዋሪው ሀሮን ላይ 7፣በሀረለጎ 6 በአጨዳ ላይ የነበሩ፣ አጎራባች በሆነው አሙሩ ወረዳም አንድ ጊዜ 18፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ 30 የሚሆኑ አማራዎች በጅምላ መገደላቸውን አውስተዋል። ከአማራ ሚሊሻዎች ጋር ሆነው 2 የኦሮሞ ተወላጅ ሚሊሻዎች ብቻ የተከፈተውን ተኩስና ግድያ ለመመከት ጥረት ማድረጋቸው ተገልጧል። ኦነግ ሸኔ ከታህሳስ 15 እስከ 17 ቀን 2013 ዓ.ም ለተከታታይ 3 ቀናት እስከ 60 የሚደርሱ ተባባሪዎቹን ይዞ ከቀኑ 10 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ደረስ እየተሰበሰበ መሆኑን በመግለፅ ለጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ መስተዳድር እና ለልዩ ሀይሎች ብንደውልም ጩኸታችንና ጥሪያችን ባለመስማት ወረዳው ነው ያስፈጀን ብለዋል፤ ልዩ ሀይሉም ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አለው ሲሉም አክለዋል። የደርጌ ኮትቻ ቀበሌ ሊቀመንበርም ከአካባቢው ሸሽተው ከመሄዳቸው ባሻገር ስልክ አያነሱልንም፤ በአካባቢው ያሉ አንዳንድ የገዳ ሽማግሌዎችና የኦሮሞ ተወላጆች ጩኸታችን በወረዳው ተሰምቶ ምላሽ እንዳናገኝ ውሸት ነው እያሉ በማፈን እንድንገደል እያደረጉ ነው ብለዋል_ነዋሪዎቹ። በህዳር 2013 ዓ.ም ከብቶቹን በኦነግ ሸኔ የተዘረፈ አንድ የሰቀላ ወረዳ አማራ ለወረዳ ሄዶ በማመልከቱ ለምን ያመለክታል በሚል ተከታትሎ ወደ ወረዳው ፍ/ቤት በማቅናት ለመግደል ሲሞክር ከልዩ ሀይል በተተኮሰ ጥይት ተገድሏል። የተገደለው የኦነግ ሸኔ ታጣቂም የአንድ የልዩ ሀይል ወንድም ሆኖ መገኘቱንና እንዲቀበር መደረጉ ተገልጧል። ለታጣቂዎች ስንቅና ትጥቅ ከሚያቀብሉት በተጨማሪ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል አባላት እየተባበሯቸው ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገልፀዋል። ነዋሪዎችም መንግስት የመከላከያ ሰራዊት እንዲልክላቸው ካልሆነም በቂ ስልጠና እና ግብአት እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርበዋል። የተገደሉት 13 አማራዎችም ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ደርጌ ኮቲቻ ቀበሌ ቦርቦር ቁራቴ በተባለ የሙስሊሞች የመቃብር ስፍራ ይፈፀማል ተብሏል። ከአካባቢው ሸሽተዋል የተባሉት የደርጌ ኮቲቻ ቀበሌ አስተዳዳሪን በእጅ ስልካቸው በመደወል ያገኘናቸው ቢሆንም ገና እያጣራን ነው በማለት ለጥያቄያችን ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ከነዋሪዎች ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply