አሳዛኝ ሰበር ዜና! በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጅ በተባለ ቀበሌ በሚኖሩ አማራዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ከታህሳስ 13 ለ14 ንጋት ጀምሮ እየተፈፀመ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ……

አሳዛኝ ሰበር ዜና! በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጅ በተባለ ቀበሌ በሚኖሩ አማራዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ከታህሳስ 13 ለ14 ንጋት ጀምሮ እየተፈፀመ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ……

አሳዛኝ ሰበር ዜና! በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጅ በተባለ ቀበሌ በሚኖሩ አማራዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ከታህሳስ 13 ለ14 ንጋት ጀምሮ እየተፈፀመ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ… ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጅ በተባለ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ አማራዎች የመከላከያ ልብስ በለበሱ የጉምዝ ታጣቂዎች የጥቃቱ ሰለባ እየሆኑ እንደሚገኙ ከግድያና ከአፈና ያመለጡ አማራዎች ተናግረዋል። በኩጅ የተባለችው የገጠር ከተማ ስትሆን ታህሳስ 13 ለ14 ቀን 2013 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ የቡድን መሳሪያ በታጠቁና የመከላከያ ዩኒፎርም በለሱ የጉምዝ ታጣቂዎችና ተባባሪዎቻቸው ከበባ ስር ሆኗለች፤ በስፍራውም አማራን እየለዩ እያጠቁ ነው፤ ቤትና ሀብት ንብረትን በእሳት እያጋዩ ስለመሆኑ ነው አሚማ ያነጋገራቸው ከአደጋው የተረፉ ምንጮች ያረጋገጡት። ደካማ እናታቸውንና መላ ቤተሰባቸውን ጥለው በታጣቂዎች ከተፈፀመባቸው ጥቃት ስለማምለጣቸው ነው ምንጫችን የነገሩን። የፌደራልም ሆነ የአማራ ክልል መንግስት በአስቸኳይ በስፍራው ደርሶ ያለበደላቸው እየተጨፈጨፉ ያሉ ወገኖችን እንዲያተርፍ ጠይቀዋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል በቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ እየተፈፀመ ነው የተባለው ማንነት ተኮር ጥቃት እውነት መሆኑን ከቡለን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ከአቶ ግዛት ነሲ ጋር በስልክ ካደረገው ቆይታ ለማረጋገጥ ችሏል። አቶ ግዛት ነሲ በበኩላቸው ከበኩጅ ቀበሌ አስተዳዳሪ የደረሰኝ መረጃ ነው በሚል የጉምዝ ታጣቂዎች ከሌሊት ጀምሮ ቀይ በሚሏቸው ነዋሪዎች ላይ አነጣጥረው ግድያ፣ማፈናቀልና ቃጠሎ እየፈፀሙ መሆኑን ሰምቻለሁ ብለዋል። መተከል ዞን ዛሬ በሚደረገው ስብሰባ ለመሳተፍ በፀጥታ አካካላት ታጅበን እየተጓዝን ሳለን ነው የድረሱልን ጥሪው የደረሰን ብለዋል። ወደ ዞን ለስብሰባ እየተጓዙ ስለመሆኑ መረጃው ቀድሞ ለታጣቂዎች መድረሱን ተከትሎ ጥቃቱን ፈፅመውት ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው መረጃው ከደረሰን ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው ያሉ የመከላከያ ሰራዊትና የሚሊሻ አባላትን ጥቃቱ ወደሚፈፀምበት ቀጠና እንዲያቀኑ እያደረግን ነው፤ አሁንም መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በአስቸኳይ ተጨማሪ ኃይል በማሰማራት ዜጎችን የመታደግ እርምጃ እንዲወስድ ሲሉ ጥሪ ያደረጉት። ይሁን እንጅ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓም ረፋድ 4 ሰዓት ተኩል ድረስ የተላከው የፀጥታ አካል የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑት ወገኖች አለመድረሱን እና ጥቃቱም ስለመቀጠሉ ነው ከዋና አስተዳዳሪው ለማረጋገጥ ተችሏል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከአደጋው ከተረፉት የቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ ነዋሪና ከወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ከአቶ ግዛት ነሲ ጋር ያደረገውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply