አሳዛኝ ሰበር ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን በሊሙ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና ተባባሪዎቹ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ በፈፀሙት ጥቃት 9 አማራዎች ሲገደሉ፣ 7 ቆስለዋል፣ በርካቶች ደግሞ ታግተው…

አሳዛኝ ሰበር ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን በሊሙ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና ተባባሪዎቹ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ በፈፀሙት ጥቃት 9 አማራዎች ሲገደሉ፣ 7 ቆስለዋል፣ በርካቶች ደግሞ ታግተው…

አሳዛኝ ሰበር ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን በሊሙ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና ተባባሪዎቹ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ በፈፀሙት ጥቃት 9 አማራዎች ሲገደሉ፣ 7 ቆስለዋል፣ በርካቶች ደግሞ ታግተው ስለመወሰዳቸው ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በሊሙ ወረዳ ነዋሪ በሆኑ አማራዎች ላይ የኦነግ ሸኔና ተባባሪዎቻቸው በፈፀሙት ጥቃት 9 ሰዎች ሲገደሉ 7 መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ህዳር 21ለ22 ቀን 2013 ዓም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ከ20 ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና ተባባሪዎቹ በአማራዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈፅመዋል። በሊሙ ወረዳ አርቁምቢ መንደር 2 በተባለ አካባቢ በተፈፀመው አማራ ተኮር ጥቃት እስካሁን በደረሰን መረጃ መሰረት 8 አማራዎች ወዲያውኑ፣ 1 ደግሞ ሆስፒታል ከገባ በኋላ በድምሩ 9 ንፁሀን ሲገደሉ 7 ቆስለዋል። በሊሙ ወረዳ ከተገደሉት መካከል ቀናው ሰጠኝ የተባለ ነዋሪ ከሌሊቱ 6:20 ላይ የመኖሪያ ቤቱና የጤፍ ክምሩ ሲቃጠል ሲወጣ ወዲያውኑ በጥይት የተገደለ ሲሆን ይህን ተከትሎም በርካቶች እሳቱን ለማጥፋት ከቤታቸው ሲወጡ ነው ጥቃቱ የተፈፀመባቸው ተብሏል። በተመሳሳይ በምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ወረዳ በዋጃ አካባቢ 18 የሚሆኑ አማራዎች ታግተው ወደ ጫካ ተወስደዋል። ለአማራ እና ለኦሮሚያ ድርጅት ጽ/ቤት መረጃውን ማድረሳቸውን የገለፁት ነዋሪዎች ወደ አካባቢው ያቀኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላትም ከአቅማችን በላይ ነው በሚል ታጋቾችን እስካሁን ማስለቀቅ አለመቻላቸውን ተናግረዋል። ህዳር 21 ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ በዋጃ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ አማራዎችን ሰብስበው ካገቱ በኋላ ከዋጃ ወደ ጉትን የሚሄድ አንድ የአማራ መኪናንም ማቃጠላቸው ተነግሯል። የአካባቢውን የመስተዳድር አካላትን እንዳገኘን ተጨማሪ መረጃ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply