
አሳዛኝ ዜና‼️ በትራፊክ አደጋ 15 የመደወላቡ ዩንቨርሲቲ መምህራን ህይወታቸው አለፈ‼️ ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ የመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከሚገኝበት ሮቤ ከተማ ወደ ዶዶላና አዳባ ካምፓሶች ለማስተማር ሲጓዙ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 15 ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መምህራን ህይወታቸውን አጥተዋል። 50 ሰው ባሳፈረ አውቶቡስ ሲጓዙ የነበረ ሲሆን ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች በተጨማሪ 20 ሰዎች ክፉኛ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሮቤና ሻሸመኔ ሆስፒታል ተልከዋል። መምህራኑ የርቀት ተማሪዎች የሆኑ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፣ የስፖርት ፣የጤናና የግብርና ትምህርት ክፍሎች ተማሪዎች ለማስተማር እያቀኑ እንደነበር በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎችና የመምህራን ጉዳዮች ዲን ዶ/ር ለታ ተናግረዋል። የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርከሪው በተለምዶ ሰብስቤ ዋሻ ውስጥ ተገልብጧል።ይህው አካባቢ በተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ የሚደርስበት ነው። ተሽከርካሪው ያልተነሳ ሲሆን ክሬን በመፈለግ ቀሪ አስክሬን ለማውጣት እየተሞከረ መሆኑን በስፍራው የሚገኙት ዶ/ር ለታ ጨምረው አስረድተዋል። (ብስራት ሬዲዬ/ ስምኦን ደረጄ) “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post