You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! መከላከያ በቡድን መሳሪያ ከታገዘው ኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጥቃት ታድጎት የነበረውን ሙሉቀን አንተነህ የተባለ የጉትንን ወጣት ለፖሊስ አሳልፎ መስጠቱ ቤተሰቦቹን ለከፍተኛ ጭንቀት ዳር…

አሳዛኝ ዜና! መከላከያ በቡድን መሳሪያ ከታገዘው ኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጥቃት ታድጎት የነበረውን ሙሉቀን አንተነህ የተባለ የጉትንን ወጣት ለፖሊስ አሳልፎ መስጠቱ ቤተሰቦቹን ለከፍተኛ ጭንቀት ዳር…

አሳዛኝ ዜና! መከላከያ በቡድን መሳሪያ ከታገዘው ኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጥቃት ታድጎት የነበረውን ሙሉቀን አንተነህ የተባለ የጉትንን ወጣት ለፖሊስ አሳልፎ መስጠቱ ቤተሰቦቹን ለከፍተኛ ጭንቀት ዳርጓል፤ አፋር ግንባር የሚሰሩ የመከላከያ አባል ሰላማዊና ሀገር ወዳድ ወንድሜ በአስቸኳይ ይለቀቅልኝ ሲሉ ጠይቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ወጣቱ ሙሉቀን አንተነህ ይባላል። በምስራቅ ወለጋ ዞን የአንገር ጉትን ከተማ ነዋሪ ነው። በግል ታጣቂነት ተሰልፎ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ላይ እርምጃ ውሰዱ በማለት በተለያዩ ግንባሮች አሰልፎት አመርቂ ውጤት ያስመዘገበ እና በጀግንነቱ የተመሰከረለት ስለመሆኑ ተነግሮለታል። ነገር ግን ይህ የጀግንነት አቋም እና አካሄዱ ቢሮ ላይ ሆነው ደመወዝ በሚቀበሉ ኦነጋዊያን ዘንድ የሚዋጥ ሆኖ አልተገኘም። ጀግናው ወጣት ሙሉቀን አንተነህን ለመግደል ሲፈልጉ የከረሙ እነዚህ አካላት ህዳር 24/2015 የተከፈተውን ጦርነት እንደ መልካም አጋጣሚ ሊጠቀሙበት ፈልገው አልተሳካላቸው ነበር። ይሁን እንጅ ህዳር 25/2015 በኮማንደር ኩምሳ የተመራው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ የኦሮሚያ ፖሊሶችና ሚሊሾች በወጣቱ ታጋይ ሙሉቀን አንተነህ መኖሪያ ቤት ላይ የዲሽቃ፣ የቦምብ እና የጥይት ማዕት አወረዱበት። የከበባ ጦርነት በተከፈተበት ጉትን በሚገኘው የሙሉቀን ቤት ውስጥም ሙሉቀንን ጨምሮ፣ ባለቤቱ አለም ጸሀይ፣ እድሜው 9 ዓመት የሆነው በህመም እየተሰቃዬ ያለ ልጃቸው፣ ሌሎች ሁለት ህጻን ልጆች እንዲሁም ሁለት እንግዶች በድምሩ 7 ሰዎች ይገኙበት ነበር። ይህን ሙሉ ቤተሰቡን ለመጨረስ ያለመውን መንግስት መር ጥቃት በቅርብ ርቀት የተመለከተው አባ ባንቲ ስንሻው ለመከላከያ መረጃ ያደርሳሉ። መከላከያም ወዲያውኑ በመድረስ ተኩሱን በማስቆም እነ ሙሉቀን አንተነህንና ቤተሰቦቹን ከጭፍጨፋ በመታደግ ሙሉቀንና ጠቁሞ ህይወታቸው እንዲተርፍ ያደረገውን አባ ባንቲ ስንሻውንና ሌሎችን ጨምሮ በእስር መልክ ለሶስት ቀናት አቆይቷል። ይሁን እንጅ በሶስተኛው ቀን ወጣቱን ታጋይ ሙሉቀን አንተነህን ከቤተሰቦቹ እና ከታሰሩ ጓደኞቹ በመነጠል ምንም እንኳ የጉትን አማራ ከፍተኛ ተቃውሞ ቢያነሳም ለጉዳዩ ጀሮ ዳባ ልበስ በማለት ወደ ነቀምት እንዲወሰድ አድርጓል። አባ ባንቲን ጨምሮ ሌሎች በርካታ አማራዎችን ግን ካልገደልናቸው በሚል ሲገለገሉ እና በአማራ ላይ በቡድን መሳሪያ የታገዘ ጦርነት ለከፈቱት ለአንገር ጉትን ፖሊሶች አሳልፎ መስጠቱ ብዙዎችን አሳዝኗል። አሁን ላይ ከ200 በላይ አማራዎች ከጉትን እና ከአንዶዴ ዲቾ እየተወሰዱ በግፍ እስር ላይ ይገኛሉ፤ በህይወት ይኑሩ ወይም አይኑሩ በትክክል ለማወቅ እየተቸገሩ መሆናቸውን ነዋሪዎች ለአሚማ ተናግረዋል። ለመጠየቅ የሚሄድ ወንድ ከተገኘ ይታሰራል የሚሉት ምንጮች አሁን ላይ ሴቶችን ጨምሮ የአፈና እስሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ታህሳስ 19 እና 21/2015 በግፍ ከታሰሩት የአማራ ሴቶች መካከል:_ 1) ቃል ኪዳን አባተ፣ 2) አታለል ጫኔ፣ 3) ካሳነሽ አበረ፣ 4) ድንቄ አየለ እና ሌሎች ስማቸው ያልታወቁ ሴቶች ስለመታሰራቸው ተገልጧል። በእነ ኮሎኔል አየነው አበበ የሚመራው መከላከያ ሰራዊት እነ ሙሉቀን አንተነህን ከጥቃት የታደገ ቢሆንም ኮሎኔል አባይ ለተባሉ ተቀይረው ለመጡ የመከላከያ አመራር አስረክበው ወደ ምዕራብ ወለጋ ዞን መቀየራቸው ተገልጧል። ሙሉቀን አንተነህም ምንም የሰራው ወንጀል ባለመኖሩ ለአንድ ወር ገደማ ከመከላከያ ጋር መቆዬቱን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የተናገሩት መቶ አለቃ አዲሱ ልዬው የተባሉ በአፋር ግንባር በመከላከያነት እየሰሩ መሆናቸውን የገለጹት የሙሉቀን ወንድም ናቸው። መቶ አለቃ አዲሱን ጨምሮ መላ ቤተሰቡ ታህሳስ 22/2015 የሰሙትን ለማመን ተቸግረዋል። “ምንም ወንጀል የለበትም፤ ለደህንነቱ ከእኛ ጋር ይቆይ” እያሉ ይዘውት የቆዩትን የጉትኑን ጀግና ወጣት ሙሉቀን አንተነህን ለጉቶጊዳ ወረዳ ፖሊስ የማስረከባቸው አሳዛኝ ዜና ተነግሯቸዋል። ለሀገር ሰላም በሚል በአፋር ግንባር እየሰሩ እንደሚገኙ የገለጹት መቶ አለቃ አዲሱም ለኮሎኔል አባይ ሲደውሉ በቂ መረጃ ለማግኘት አልቻሉም። ነገር ግን ከአንድ ዐይን እማኝ አመሻሹን ደርሶኛል የሚሉት መረጃ ሙሉቀን አንተነህ በጉቶጊዳ ፖሊስ በካቴና ታስሮ ስለመዋሉ ይናገራሉ። በነቀምት አንድ ወር ገደማ በመከላከያ ተይዞ የቆየው የአንገር ጉትኑ ወጣት ሙሉቀን አንተነህ ለፖሊስ ተላልፎ መሰጠቱ እንዳሳዘናቸው የተናገሩት መቶ አለቃ አዲሱ አካሄዱን በማውገዝ ከግፍ እስር በአስቸኳይ እንዲለቀቅላቸው ጥሪ አድርገዋል። ወንድሜን እንዳይገድሉብኝ የሚል ስጋት እንዳላቸው ያልደበቁት መቶ አለቃ አዲሱ አይደለም ሞት በአካሉም ሆነ በስነ ልቦና ምንም ዓይነት ጉዳት ሊደርስበት የማይገባ ሰላማዊ እና ሀገር ወዳድ ጀግና ነው ብለውታል። ይህን ቅሬታ በመያዝ አሚማ በምስራቅ ወለጋ ዞን የመከላከያ መምሪያ አዛዥ ናቸው ለተባሉት ለኮሎኔል አየነው አበበ ቢደውልም ከማስፈራራት ያለፈ ቀና መልስ ሊያገኝ አልቻለም። ጋዜጠኛ ከሆንክ ከቦታው መጥተህ ስራ፣ በአካል እንጅ ሳንተዋወቅ በስልክ የሚሰጥ መረጃ የለም ያሉት ኮሎኔል አየነው መጨረሻ ላይ ግን ወደሌላ አካባቢ መቀየራቸውን ሳይገልጹ አላለፉም። ሌላኛው ቤተሰብ እንደሚለው ምንም ወንጀል ያልፈጸመን ሰው ከእነ ኮሎኔል አየነው ተረክበው ከቆዩ በኋላ ለጉቶጊዳ ፖሊስ አሳልፈው ሰጥተዋል ለተባሉት ለኮሎኔል አባይ በተደጋጋሚ ብንደውልም የሚጠራ ስልካቸውን እንኳ ለማንሳት አልፈቀዱም። አሚማ ሙሉቀን አንተነህን ከመከላከያ ተቀብሏል ለተባለው በምስራቅ ወለጋ ዞን ለጉቶጊዳ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ለኢንስፔክተር በንቲ ደውሎ ያገኛቸው ቢሆንም እረፍት ከወጣሁ ሶስት ቀን ሆኖኛል፤ የምትሉት ሰው በፖሊስ ጣቢያ ስለመግባቱ ለጊዜው የማውቀው መረጃ የለኝም ሲሉ ነው ምላሽ የሰጡት። ባለቤቷ ወረዳው ላልሆነ እና ለማያውቀው አካል ለጉቶጊዳ ተላልፎ የተሰጠባት እና ከእነ ልጆቿ በጥይት አረር እና በቡድን መሳሪያ ተኩስ ጣራው፣ ቆርቆሮው እና ግድግዳው ከተበሳሳው መኖሪያ ቤታቸው የተረፈችው አለም ጸሀይም ወደ ቤት ተወርውሮ ገና ያልፈነዳ እና ያልተነሳ ቦምብ በመኖሩ እንዲሁም ከጎሳ እሳቤ ወጥቶ የሚያግዛት አመራር ባለመኖሩ ከእነ ታማሚው እና ሌሎች ልጆቿ ጋር ያለማንም ጠያቂ በዘመድ ቤት ተጠግታ የመከራ ህይወት ለመግፋት መገደዷን ለማወቅ ተችሏል። በቅርቡ በሴት አማራዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው እስር እንዳለ ሆኖ ከ200 በላይ አማራዎች በግፍ የታሰሩባቸው እና በአግባቡ በቤተሰብ የማይጠየቁባቸው አንገር ጉትን እና አንዶዴ ዲቾ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆናቸው ወንድ የአማራ ልጆች ከሚሳደዱባቸው አካባቢዎች መካከል ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply