You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! በመተማ ወረዳ አስከፊው የእገታ ወንጀል ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፤ ሀምሌ 14 ቀን ከቋራ ወደ ጎንደር በተሽከርካሪ ሲመለሱ በነበሩ አማራዎች ላይ የቅማንት ተወላጅ የሆኑ ሽፍቶች…

አሳዛኝ ዜና! በመተማ ወረዳ አስከፊው የእገታ ወንጀል ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፤ ሀምሌ 14 ቀን ከቋራ ወደ ጎንደር በተሽከርካሪ ሲመለሱ በነበሩ አማራዎች ላይ የቅማንት ተወላጅ የሆኑ ሽፍቶች…

አሳዛኝ ዜና! በመተማ ወረዳ አስከፊው የእገታ ወንጀል ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፤ ሀምሌ 14 ቀን ከቋራ ወደ ጎንደር በተሽከርካሪ ሲመለሱ በነበሩ አማራዎች ላይ የቅማንት ተወላጅ የሆኑ ሽፍቶች ፈጽመውታል በተባለው ጥቃት ጎንደር ለሚሰጠው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ለመውሰድ የተዘጋጀች ተማሪ እና አንድ ጥበቃ በአሰቃቂ መልኩ ተገድለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 14/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በርሚል ቀበሌ ከሰሞኑ የተከሰተውን የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) በሽታን ተከትሎ መድኃኒትና አንዳንድ አስፈላጊ ግብአቶችን ሀምሌ 14/2015 ከጎንደር ይዘው በመውረድ ያስረከቡ ሰዎች ስለመኖራቸው ተመላክቷል። ከመተማ ወረዳ መረጃ እና ክትትል ንዑስ ክፍል ኃላፊ ዋና ሳጅን ሲሳይ ገዳሙ የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው በእለቱ ከቀኑ 10 ሰዓት ተኩል ወደ ጎንደር ሲመለሱ በመተማ ወረዳ ጉባይ መገንጠያ ለምለም ተራራ አካባቢ ጠብቀው የቆዩ በጫካ ለእገታ፣ ለግድያ እና ለዝርፊያ የሚንቀሳቀሱ የቅማንት ተወላጅ የሆኑ ሽፍቶች ተሽከርካሪው ላይ አልመው በመተኮስ ሁለት አማራዎችን ገድለዋል። ተሳፍረውበት የነበረው ታርጋ ቁጥሩ 17094 ET ኮድ 4 የሆነው የመድኃኒት ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ጋቤናም 3 ቦታ ላይ በጥይት ተመቶ መስታውቱ ረግፏል። በእለቱ በውስጡ ተሳፍረው የነበሩትም:_ 1) አስቻለው ማሬ ነበሩ (የባለሀብት ጥበቃ) እድሜ 28 የሆነውን ደረቱን በ 6 ጥይት በመምታት ገድለው፣ ቋም ክላሽ ወስደውበታል። 2) ጥሩዬ ፈጠነ ካሴ እድሜ 26 የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ ፈተናን በጎንደር ለመውሰድ እየተጓዘች የነበረች ተማሪ ስትሆን ጭንቅላቷን በ1 ጥይት በመምታት የገደሏቸው ስለመሆኑ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያገኘው መረጃ አመልክቷል። አስከሬናቸውም ወደ መተማ ሪፈራል ሆስፒታል መወሰዱን ለማወቅ ተችሏል። የ560 ሽህ ብር የአተት መድኃኒት ወስደው አስረክበው እየተመለሱ የነበሩት አንድ ቄስ እና አሽከርካሪው በአካባቢው የነበሩ አርሶ አደሮች እና በአካባቢው በነበረ የጸጥታ አካል ከግድያ እና ከእገታ መትረፋቸው ተሰምቷል። በመተማ ወረዳ ሽንፋ አካባቢ ከቀናት በፊት የታገቱት አራት ላም እረኞች እና የቋራው ወጣት ድርጅት ዱሬ ከተገደለበት ተሽከርካሪ ታግተው የተወሰዱ አማራዎችም በድምሩ ከ1 ሚሊዮን ብር ከፍለው መለቀቃቸውን ምንጮች ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከአጋቾች ጋር በመመሳጠር በእገታ እና በዝርፊያ ከሚገኘው ጥቅም የሚጋሩ አንዳንድ የወረዳ እና የዞን አመራሮች እጅ እንዳለበት አመላካች ነው። አጋቾች ሲያዙም በሚኖሩ ጫናዎች እና በብልሹ አሰራር ጭምር በአጭር ጊዜ እንዲለቀቁ ስለሚደረግ የእገታ ወንጀል ዋና የገቢ ምንጭ ያደረጉ አካላት መኖራቸው ተገልጧል። በዞኑ በየሳምንቱ በሚባል ደረጃ ቢያንስ ከአስር በላይ የሚሆኑ ሰላማዊ ወገኖች፣ አርሶ አደሮች፣ ነጋዴዎች፣ የቀን ሰራተኞች እና ላም እረኞች እየታገቱ ዘርፈ ብዙ ግፍ እና በደል እንደሚደርስባቸው ከአካባቢው ያነጋገርናቸው ተቆርቋሪዎች ተናግረዋል። ህዝቡ ማንንም መጠበቁን ትቶ እርስ በርስ በመመካከር ራሱን ብሎም ወገኑን ከአስከፊው እገታ፣ ግድያ እና ዝርፊያ እንዲታደግ ጥሪ ቀርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply