You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! በመተማ ወረዳ አኩሸራ በተባለ ቀበሌ ከአንድ ሳምንት በፊት በታጣቂዎች ታግተው ወደ ጫካ የተወሰዱ 4 አማራዎች ታጋቾችን ለማስለቀቅ ቤተሰብ የተጠየቀውን 850 ሽህ ብር ከከፈለ በ…

አሳዛኝ ዜና! በመተማ ወረዳ አኩሸራ በተባለ ቀበሌ ከአንድ ሳምንት በፊት በታጣቂዎች ታግተው ወደ ጫካ የተወሰዱ 4 አማራዎች ታጋቾችን ለማስለቀቅ ቤተሰብ የተጠየቀውን 850 ሽህ ብር ከከፈለ በ…

አሳዛኝ ዜና! በመተማ ወረዳ አኩሸራ በተባለ ቀበሌ ከአንድ ሳምንት በፊት በታጣቂዎች ታግተው ወደ ጫካ የተወሰዱ 4 አማራዎች ታጋቾችን ለማስለቀቅ ቤተሰብ የተጠየቀውን 850 ሽህ ብር ከከፈለ በኋላ በጥይት ተገደሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)… ሀምሌ 3/2015 ዓ/ም_ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ አኩሸራ በተባለ ቀበሌ ተነስተው ከመቸላ በተባለ አካባቢ ሀዘን ለመድረስ በሚል ሰኔ 24/2015 በእግር እየተጓዙ በነበሩ 7 አማራዎች የቅማንት ተወላጅ በሆኑ ታጣቂዎች ስለመታገታቸው መረጃ አጋርተን ነበር። በእለቱም ከመካከላቸው ሁለቱን በጥይት ሲገድሉ፣ አንደኛው ነዋሪም ቆስሎ በመትረፉ ወደ ህክምና መግባቱን፤ ነገር ግን ቀሪ አራት የሚሆኑ ታጋቾችን በጠራራ ጸሀይ አፍነው ወደ ጫካ ስለመውሰዳቸው ተገልጾ ነበር። እገታው በተፈጸመበት ወቅትም:_ 1) ቄስ አበጀ ሀጎስ እድሜ 45 የሆነ እና 2) ታደሰ ደርሶ የተባሉ የ60 ዓመት የእድሜ ባለ ጸጋ የሆኑት ነዋሪዎች እያንዳንዳቸው በ3 ጥይት ተመተው ተገድለዋል። አቶ አስቻለው ተጌ የተባለ ነዋሪ ደግሞ የቀኝ ትክሻውን በ1 ጥይት ተመቶ ቆስሎ በማምለጡ በገንዳውሃ የህክምና እገዛ እየተደረገለት ይገኛል። ሀምሌ 3/2015 ለአሚማ የደረሰው አሳዛኝ መረጃ እንዳመለከተው ግን በእነዚህ የቅማንት ተወላጅ የሆኑ ታጣቂዎች ታግተው ወደ ጫካ የተወሰዱት አራቱ ሰዎች በድምሩ 850 ሽህ ብር ከከፈሉ በኋላ በጥይት ተገድለዋል። በጭፍን ጥላቻ ታውረው ለሰፊው የአማራ ህዝብ ከጠላትም በላይ ጠላት በመሆን ማንነቱን እንደወንጀል እየቆጠሩ ያሉ እነዚህ ታጣቂዎች የህወሓትንና የኦነግን ጸረ አማራ እና ጸረ ኢትዮጵያ አቋም እና አላማን በተለይም በመተማ፣ በቋራ፣ በአዳኝ አገር ጫቆ (ነጋዴ ባህር) እና በአርማጭሆ አማራዎች ላይ በግልጽ እየተገበሩት ስለመሆኑ ቢያንስ በየሳምንቱ በሚባል ደረጃ የሚፈጽሙት ጥቃት ግልጽ ማሳያ ስለመሆኑ ብዙዎች ይገልጻሉ። ከአንድ ሳምንት የእገታ ቆይታ በኋላ በቤተሰብ ለምኖ የተጠየቀውን ገንዘብ የከፈለ መሆኑ ቢታወቅም የአረመኔዎች ተልዕኮ ፈጻሚ የሆኑት ግልገል አረመኔዎች ሀምሌ 3/2015:_ 1) ቄስ ተገን ሽበሽ፣ 2) አንዱ ዓለም አሰፋ፣ 3) አይቶ አጣናው እና 4) ተስፋሁን አባታለም የተባሉ በአኩሸራ ቀበሌ የኩመር ከተማ ነዋሪዎችን መቃ በተባለ ቀበሌ በማሰንበት በጥይት መግደላቸው ታውቋል። በአጠቃላይ 6 ገበሬዎችን ሲገድሉ 1 ቆስሎ በህክምና ክትትል ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀደመ መጠይቁ አሚማ ያነጋገራቸው በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ የፖሊስ መረጃ ክፍል ዋና ሳጅን ሲሳይ ገዳሙ የጭካኔ ግድያ እና እገታ የፈጸሙ አካላት ሰኔ 1/2015 በመተማ ወረዳ መቃ በተባለ ቀበሌ የሚኖሩ የቅማንት ተወላጅ የሆኑ ግለሰቦች በጫካ በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ አማራዎች ተገድለውብናል በሚል በማያውቁት ነገር በስመ አማራ በጅምላ የተፈጸመባቸው ግድያ ስለመሆኑ በመግለጽ ጉዳዩን ደም ምለሳ ከሚል ጎጅ ባህል ጋር ማያያዛቸው ይታወሳል። በየጫካው እየተንቀሳቀሱ የጸረ አማራዎችን ተልዕኮ እየፈጸሙ ያሉ ታጣቂዎች ከግንቦት እስከ ሀምሌ መግቢያ 2015 ድረስ ከፈጸሟቸው አሰቃቂ ግድያዎች መካከልም:_ 1) በመተማ ወረዳ ሽንፋ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሽኩርያ በተባለ አካባቢ ሰኔ 6/2015 ከቀኑ 12 ሰዓት ገደማ በእርሻ ማሳቸው ላይ:_ 1) ሞገስ ፍቃዴ፣ 2) አራጌ ደርሶ እና 3) አየሁ ሽባባው የተባሉ ጀግና አራሽ እና ተኳሽ ወጣቶችን ገድለዋል። 2) ከሽንፋ በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ማጠቢያ በተባለ አካባቢ ደግሞ ሰኔ 10/2015 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ገደማ ደግሞ ዲያቆን ጌጤ ጥላሁን የመካነ ህይወት ሽንፋ ማርያም አገልጋይን በጥይት ገድለዋል። 3) ሀምሌ 1/2015 ከቀኑ 9 ሰዓት ጉባይ እና ለምለም ተራራ አዋሳኝ አካባቢ በማገት ድርጅት ዱሬ የተባለ የቋራ ተወላጅ ምሁሩን በመግደል ሰባት አማራዎችን አግተው ወደ ጫካ መውሰዳቸው እንደ አብነት ይጠቀሳሉ። በመጨረሻም በጎንደር የቋራ፣ የመተማ፣ የአዳኝ አገር ጫቆ፣ የአርማጭሆ እና የአካባቢው ማህበረሰብ ጀግንነቱን፣ ወጉንና ባህሉን ከማይመጥን እና ከሚያጎድፍ ገንዘብ ለምኖ ለተላላኪ አጋቾች ገንዘብ ከመክፈል እና ከአገዛዝ ጠባቂነት በመውጣት እንደለመደው በራሱ ህዝባዊ መንገድ የገጠመውን ፈተና እንዲወጣ በተደጋጋሚ ጥሪ ቀርቦለታል። በግፍ እየተገደሉ ያሉ ንጹሃን ወገኖቻችንን ነፍስ ይማር! ለመላው ቤተሰቡ መጽናናትን እንመኛለን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply