You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! በመተማ ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች ጫካ በሸፈቱ የቅማንት ታጣቂዎች እየተፈጸመባቸው ባለው ተከታታይ የእገታ፣ የዝርፊያና የግድያ ወንጀል የተነሳ በቀያቸው ሰርተው ለመብላትና ኑሮአቸው…

አሳዛኝ ዜና! በመተማ ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች ጫካ በሸፈቱ የቅማንት ታጣቂዎች እየተፈጸመባቸው ባለው ተከታታይ የእገታ፣ የዝርፊያና የግድያ ወንጀል የተነሳ በቀያቸው ሰርተው ለመብላትና ኑሮአቸው…

አሳዛኝ ዜና! በመተማ ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች ጫካ በሸፈቱ የቅማንት ታጣቂዎች እየተፈጸመባቸው ባለው ተከታታይ የእገታ፣ የዝርፊያና የግድያ ወንጀል የተነሳ በቀያቸው ሰርተው ለመብላትና ኑሮአቸውን ለመምራት በእጅጉ መቸገራቸውን ገልጸዋል፤ ዛሬም እንደተለመደው አንድ ነጋዴን በጥይት በመግደል ሰባት አማራዎችን አግተው ወደ ጫካ መውሰዳቸው ተሰምቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 1/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ፣ ቋራ፣ አዳኝ አገር ጫቆ እና አካባቢው የሚኖሩ አማራዎች በጫካ በሚንቀሳቀሱ የቅማንት ታጣቂዎች አማካኝነት በተለይም በሽንፋ፣ ሻሽጌ፣ ጉባይ ጀጀቢት፣ ኮዘራና በደላ እንዲሁም ሌንጮ በሚባሉ አካባቢዎች እየተፈጸመባቸው ባለው ተከታታይ የግድያ፣ የእገታ እና የዝርፊያ ወንጀል የተነሳ ነግደው፣ አርሰው እና አልምተው በቀያቸው ለመኖር መቸገራቸውን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ገልጸዋል። ለራሳቸው ደህንነት መጠበቂያ የሚሆን ጦር መሳሪያቸውን ይዘው እንዳይንቀሳቀሱ የሚከለክለው የአገዛዙ ጦር ከግድያ፣ ከእገታ እና ከዝርፊያ ሊታደጋቸው እንዳልቻለ በመግለጽ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛል። ሀምሌ 1/2015 ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ ከሽንፋ ገቢያ ውለው ወደ ገንዳ ውሃ በአይሱዙ መኪና እየተጓዙ በነበሩ ረዳቱን ጨምሮ በ7 አማራዎች ላይ በእኒሁ የተደራጁ እና በጫካ በሚንቀሳቀሱ የቅማንት ታጣቂዎች አማካኝነት የእገታ ወንጀል ተፈጽሟል። ከመካከላቸውም 8ኛ ታጋች የሆነውን ነጋዴ ደግሞ ጆሮው ላይ በጥይት ደብድበው በመምታት ገድለው ጥለውት ተገኝተዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ይህ እገታ የተፈጸመው በጉባይ እና ለምለም ተራራ አዋሳኝ አካባቢ በጫካ ይንቀሳቀሳሉ በተባሉ የቅማንት ተወላጅ በሆኑ የሽፍታ ቡድን አባላት ነው። ወድቆ የተገኘውን አስከሬኑን የለምለም ተራራ አካባቢ ነዋሪዎች እንዲነሳ በማድረግ ወደ ገንዳውሃ ከተማ መላካቸውን ለአሚማ ተናግረዋል። አሽከርካሪው ግን ከተፈጸመው ጥቃት ተርፎ በሸለቆ ውስጥ ገብቶ ስለማምለጡ ታውቋል። ታግተው ከተወሰዱት መካከል መለስተኛ ባለሃብቶች እንደሚገኙበት የአሚማ ምንጮች ገልጸዋል። ከታገቱት መካከልም የሽንፋ፣ የቋራ እና የሌላም አካባቢ ነዋሪዎች ይገኙበታል ተብሏል። በመተማ ወረዳ አሁን ላይ ከ200 እስከ 250 የሚሆኑ የህወሓት ተልዕኮ ፈጻሚ ናቸው የተባሉ የቅማንት ተወላጅ የሽፍታ ቡድን አባላት ሱዳን ከኢትዮጵያ በምዕራብ ጎንደር በኩል በወረራ በያዘችው አካባቢ በመንቀሳቀስ የስልጠና እና የቁሳቁስ ድጋፍ በማግኘት አማራውን በሁለንተናዊ መልኩ የማጎሳቆል ተግባራቸውን አጠናክረው የቀጠሉበት ስለመሆኑ ነዋሪዎች በምሬት ይናገራሉ። በመተማ ወረዳ የሽንፋ እና የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት እነዚህ ታጣቂዎች በግንቦት እና በሰኔ 2015 ዓ/ም ብቻ ከፈጸሟቸው አስከፊ ጸረ አማራ የእገታ ወንጀሎች መካከል:_ 1) በግንቦት ወር ሁለተኛ ሳምንት 2015 ዓ/ም ከሽንፋ ወደ ገጠር ቀበሌ ሲደረግ በነበረ ጉዞ ላይ ተሳፍረው የነበሩ አሽከርካሪ፣ ረዳት እና ተሳፋሪን በማገት 475 ሽህ ብር ተቀብለው ለቀዋቸዋል። 2) በሽንፋ ሽኩርያ በሚባል አካባቢ በእርሻ ማሳ ላይ የነበሩ አንድ አባት ከሁለት ልጆቻቸው ጋር በማገት በመጀመሪያ 1 ሚሊዮን ብር፣ ከዛም 600 ሽህ ብር በስተመጨረሻም በድርድር 320 ሽህ ብር ከፍለው ግንቦት 30/2015 መለቀቃቸው ታውቋል። 3) በመተማ ወረዳ ሽንፋ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሽኩርያ በተባለ አካባቢ ሰኔ 6/2015 ከቀኑ 12 ሰዓት ገደማ በእርሻ ማሳቸው ላይ የነበሩ:_ 1) ሞገስ ፍቃዴ፣ 2) አራጌ ደርሶ እና 3) አየሁ ሽባባው የተባሉ ጀግና አራሽ እና ተኳሽ ወጣቶችን በጥይት መግደላቸው፣ 4) በተጨማሪም ከሽንፋ በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ማጠቢያ በተባለ አካባቢ ደግሞ ሰኔ 10/2015 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ገደማ ደግሞ ዲያቆን ጌጤ ጥላሁን የተባለን የመካነ ህይወት ሽንፋ ማርያም አገልጋይን በጥይት መግደላቸው፣ 5) በሰኔ ወር ከመተማ እና ቋራ ወረዳ ወደ ጎንደር ሲሄዱ የነበሩ ኹለት የጭነት መኪና አሽከርካሪዎችን እና ኹለት ተሳፋሪዎችን አግተው ከወሰዱ በኋላም “እኛ የቅማንት ታጣቂዎች ነን፤ ለእያንዳንዳቸው 300 ሺህ ብር ካልከፈላችሁ እንገላቸዋለን” እያሉ የታጋች ቤተሰቦችን በስልክ ሲያስፈራሩ እንደነበር እና ታጋቾቹ እስካሁንም አለመለቀቃቸው፣ (የአዲስ ማለዳ ዘገባ)፣ 6) በሰኔ ሶስተኛ ሳምንት 2015 ዓ/ም በቋራ ወረዳ ዱባባ ከተባለ አካባቢ አግተው ጀምበርጌ በተባለ ጫካ ያሰነበቷቸውን 2 ሰዎች 800 ሽህ ብር እንዲከፍሉ ጠይቀው እንደነበር በመጨረሻም ክፍያ መፈጸሙን ተከትሎ ሰኔ 30/2015 ስለመለቀቃቸው ተነግሯል። 7) ሀምሌ 1/2015 ከቀኑ 9 ሰዓት ጉባይ እና ለምለም ተራራ አዋሳኝ አካባቢ አንድ በመግደል ሰባት አማራዎችን አግተው ወደ ጫካ መውሰዳቸውም ታውቋል። በእገታ እየተጎሳቆለ ያለው ጠረፍ ጠባቂው የመተማ፣ ሽንፋ፣ ቋራ፣ አዳኝ አገር ጫቆ እና የአርማጭሆ ህዝብ ከአገዛዙ መጠበቁን እንዲተው ተጠይቋል። አካባቢው ችሎታ እና አቅሙ ሳያንሰው መቶ በማይሞሉ የህወሓት አሽከሮች የታገተ ቤተሰቡን ለማስለቀቅ በገበያ፣ በአብያተ ክርስቲያናት እና በመስጊድ ጭምር ገንዘብ በልመና እያሰባሰበ መክፈልን ልማድ እያደረገው መምጣቱ አደገኛ አካሄድ ነው ተብሏል። በመጨረሻም ከዚህ ነባር ጀግንነቱን፣ ወጉንና ባህሉን ከማይመጥን እና ከሚያጎድፍ አሰራር በመውጣት ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣ እርምጃ በመውሰድ ለትውልዱ የሚበጅ ታሪክ እንዲያስቀምጥ ጥሪ ቀርቦለታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply